የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሳምንት መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ።የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ፕሮግራም ደግሞ ወደ ጥቅምት ሰባት መራዘሙን ፌደሬሽኑ አስታውቋል።
የፌዴሬሽኑ የውደድርና ተሳትፎ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ለኢዜአ እንደገለጹት ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ሊራዘም የቻለው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጭቃ በመሆኑ ውድድር ማስተናገድ ስለማይችልና ሌሎች የሲቲ ካፕ ውድድሮች በመኖራቸው ነው።
የሲቲ ካፕ ውድድሮች በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚደረጉ ናቸው።
በእነዚህ ምክንያቶች ሊጉ ከጥቅምት አራት ወደ ጥቅምት አስራ አንድ መራዘሙን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።
መስከረም 27 ለማካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ጥቅምት ሰባት እንዲካሄድ ተወስኗል።
በ1990 ዓም በአዲስ መልክ የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአስራ ስድስት ክለቦች መካከል የሚደረግ ነው።
ምንጭ -ኢዜአ
አስተያየት ይስጡ