ኢትዮጵያን በካፍ ኮንፈደሬሽን ዋንጫ የወከለዉ መከላከያ ስፖርት ክለብ ካሜሩን ያንግ ስፖርትስ አካዳሚ ጋር በነበረው የመጀመሪያ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ባስተናገደበት ወቅት የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ የመሩት የውደደሩ ኮሚሽነር የስቴዲየሙ መጸዳጃዎች እና መልበሻ ክፍሎች የጸዱ አይደሉም በማለት ለካፍ ሪፖርት ማድረጋቸውን ምክኒያት አዲስ አበባ ስቴዲየም ታግዷል የተባለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እና ካፍ መጸዳጃ ክፍሎቹ አዲጸዱ ማሳሰቢያ ነው የሰጠው በማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁሉም መገናኛ በዙሃን አሳወቆአል ፡፡
የአዲስ አበባ ስቴዲየም የመጸዳጃ ቤት እና የትኬት ሽያጭ ችግር ከ40 አመት በላይ ሊቀረፍ እና ሊጸዳ ያልቻለበት ምክኒያት በጣም አነጋጋሪ ነው ምናልባት ባለቤቱ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሲሆን ተጠቃሚዎቹ አትሌቲክስ እና አግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲሁም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፈቀደላቸው የተለያዩ የስፖርት እና የሀይማኖት ተቋማት ይጠቀሙበታል በተለይ በመጠቀም ደረጃ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው እግርኳስ ፌዴሬሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጊዚያዊ ሳይሆን ዘለቄታዊ መፍትኄ መፈለግ አለበት ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመገናኛ ብዙሃን የላከው ደብዳቤ
ለስፖርት መገናኛ ብዙሃን በሙሉ
የአዲስ አበባ ስታዲየም ለበርካታ ዓመታት በብቸኝነት የተለያዩ ውድድሩሮችን በከፍተኛ ጫና ከአቅሙ በላይ እያስተናገደ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የእድሳቶች እና የማስተካከያ ስራዎች እየተሰሩ ውድድሮችን እያካሄደ ቢገኝም በቅርቡ አገራችን ባስተናገደችው የኢትዮጵያው መከላከያ ከ ካሜሮኑ ያንጋ ስፖርት አካዳሚ ኮንፌዴሬሽን ካኘ ጨዋታ ወቅት የውድድሩ ታዛቢ የሰጡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መልዕክት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚገኙ ውስጣዊ ክፍሎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ መዘጋጀት እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስታዲየሙ ከኢንተርናሽናል ውድድሮች ታግዷል በሚል የተሳሳተ እና መሠረተ ቢስ የሆነ መረጃ ለሕብረተሰቡ የሚያስተላልፋት ከእውነት የራቀ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይገልፃል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
አስተያየት ይስጡ