መነሻ ገጽ Africa በአምላክ ተሰማ ተጠባቂውን የቱኒዝያን ደርቢ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ
AfricaTunis leagueአፍሪካኢትዮጵያን በውጪ

በአምላክ ተሰማ ተጠባቂውን የቱኒዝያን ደርቢ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ

አጋራ
አጋራ

ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ዛሬ 10 ስአት ላይ የሚካሄደውን የኤስፒራንስ ዲ ቱኒዝና ኤቷህል ዶ ሳህል ጨዋታ ይመሩታል።

የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዲመደቡለት የጠየቀው ጥያቄ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዘንድ ተቀባይነት አግንቶ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ እንደሚመሩ መደረጉን የወጡት መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ።በአፍሪካ እግር ኳስ በጠንካራ ተፎካካሪነታቸው ከሚጠቀሱት ክለቦች መካከል የቱኒዚያው ኢስፔራንስ ዲቱኒዝ እና ኤቷል ዶሳሂል የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ፌደሬሽኑ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባአምላክ ተሰማ እና ሁለት ረዳት ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመድብላቸው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በላኩት የትብብር ደብዳቤ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን። ጥያቄው ተቀባይነት አግንቶ በዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ይህንን ጨዋታ ሲመሩት 1ኛ ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤለ 2ኛ ረዳት ዳኛ ከግብፅ 4ኛ ዳኛ ለሚ ንጉሴ መሆናቸው ተረጋግጧል ። ዋና ዳኛው አምና በአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ በሩብ ፍፃሜ ውጥረት ውስጥ የነበረው የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ በብቃት መወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከባአምላክ በተጨማሪ የደቡብ አፍሪካው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቪክቶር ጎሜዝ ጨዋታውን እንዲመሩ ጥሪ ቢደረግላቸውም የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውድቅ አድርጓል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

“ከክለቡ ጋር ስለ መለያየት ያወራነው ነገር የለም” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የደቡብ ሱዳኑ ክለብ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ?...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ከሜሲ ጋር በአንድ ሜዳ የደመቀው የሜጀር ሊግ ሶከሩ ኮከብ ማረን ሀይለስላሴ

የማረን ሁለቱ ታናናሽ ወንድሞቹም እግር ኳስን ተጫውተዋል አሁን ላይስ ምን ላይ ናቸው።...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የእናቱን ሀገር መለያ የመልበስ ፍላጎት ያለው የግራ መስመር አጥቂ

ለአሜሪካ ከሀያ አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫወተው እና በዴንማርክ የሚገኘው ተጫዋች። እናቱ...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

“ኢትዮጵያን ባገለግል እጅግ ደስ ይለኛል” ወጣቱ ተጫዋች ጆሲሳ ስምዖን

በጀርመኑ ኮሎኝ የሚገኘው እና በቀጣዩ ክረምት ወደ ዋናው ቡድን የሚያድገው ወጣቱ የግራ...