ትውልዷም ዕድገቷም ከንባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ ሲሆን የክለብ ህይወቷ ጅማሮ ግን ሀዋሳ ከተማ ነው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪዋ እና ኮከቧ ሎዛ አበራ። ደደቢት ፣ አዳማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገር ውስጥ የደመቀችባቸው ክለቦች ሲሆኑ ወደ ሲውዲን እንዲሁም ስኬታማ ጊዜ በነበራት የማልታው ቢርኪርካራ ተጫውታ አሳልፋለች።

በአሁኑ ሰዓት ለአሜሪካው ዲሲ ፓወር በመጫወት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ እንስት በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ብትገኝም በወላጆቿ አማካኝነት ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍን ለትውልድ ሀገሯ ዱራሜ ፓይለት ፕሮጀክት በስጦታ መልክ አበርክታለች።




አስተያየት ይስጡ