መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና ሲዳማ ቡና ለቡድኑ ከፍተኛ ሽልማትን ሸለመ
ሲዳማ ቡናዜናዎች

ሲዳማ ቡና ለቡድኑ ከፍተኛ ሽልማትን ሸለመ

አጋራ
አጋራ

የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ለሆነው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በዛሬው ዕለት ለክለቡ በሀዋሳ ከተማ አቀባበል እንደተደረገለት የሚታወቅ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ ዳጎስ ያለ ሽልማት ተበርክቶለታል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፣ አቶ በየነ በራሳ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ፣ አቶ አብርሃም ማርሻሎ የክልሉ የመንግስት ተጠሪ እና የብልፅና ቢሮ ሀላፊ ፣ አቶ ጃጎ አገኘሁ የክልሉ የባህል ፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ እና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ እና ሌሎች የመንግስት ሀላፊዎች እና የክለቡ አመራሮች በርካቶች ጥሪ የተደረገላቸው እና የክለቡ አባላት በተገኙበት  ሽልማት ተበርክቷል።

ለአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እና ለረዳት አሰልጣኙ ቅዱስ ዘሪሁን እንዲሁም ለህክምና ባለሙያው ብሩክ ደበበ ሀዋሳ ከተማ ላይ የ200 መቶ ካሬ መሬት ከነ ካርታው እና የ1 ሚሊዮን ብር ሲሸለሙ  ለያሬድ ባዬ ፣ ደስታ ደሙ ፣ ብርሀኑ በቀለ ፣ ደግፌ አለሙ ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ ፣ ሬድዋን ናስር ፣ መስፍን ታፈሠ ፣ አስቻለው ሙሴ ፣ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን የ2 መቶ ካሬ መሬት እና 1 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ለቀሩት ተጫዋቾች የ2 መቶ እና የ150 ካሬ የመሬት እንዲሁም ለቀሩት የቡድኑ ተጫዋቾች ለሾፌር ለረዳት እንዲሁም ለሌሎች አካላት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

እንዲሁም ክለቡ እዚህ እንዲደርስ ላደረጉት የቀድሞው ስራ አስኪያጅ አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ የእውቅና እና የ2 መቶ ሺህ እንዲሁም ደግሞ ለክለቡ አስጨፋሪ እያሱ ሲዳ የ2 መቶ ካሬ መሬት ለክለቡ ደጋፊ ማህበር እና ለክልሉ እግር ኳስ ፌድሬሽን በተመሳሳይ የ2 ሚሊዮን ብር እና ለሌሎችም የመሬት የገንዘብ እና የሰርተፊኬት ሽልማት ከተበረከተ በኋላ መርሃግብሩ ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...