የያንግ አፍሪካዋ ቸጫዋች በስሟ ለተቋቋመ የእግር ኳስ ፕሮጀክት የትጥቅ ድጋፍን ማድረጓ ታውቋል።
ጎፋ ዞን ኦይዳ ወረዳ ሸፍቴ ከተማ ትውልድ እና ዕድገቷ ሲሆን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ደግሞ የአራት አመት የእግር ኳስ ስልጠና በአግባቡ ተከታትላ አጠናቃለች።

በሀገር ውስጥ ለመቻል እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጫወት ራሷን ለብዙሀኑ ያስተዋወቀችዋ ባለ ግራ እግሯ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመስመር አጥቂ አረጋሽ ካልሻ በትውልድ ሀገሯ በስሟ ለተቋቋመው አረግ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክት የትጥቅ ድጋፍን አድርጋለች።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በነበራት አስደናቂ አቋም ከሀምበራዊ ለባሾቹ ጋር ደጋግማ የሊግ ዋንጫን ያሳካችው እና የሴካፋ አሸናፊም ጭምር መሆን የቻለች ሲሆን ወደ ታንዛኒያ በማምራትም በያንጋ አፍሪካ ክለብ ውስጥ ያለፉትን ሁለት አመታቶች በመጫወት ላይ ትገኛለች። በያዝነው የሀገሪቱ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለችው ኢትዮጵያዊቷ ዕንስት ተጫዋች በአካባቢው ልክ እንደ እርሷ ለሀገር የሚበቁ ተጫዋቾችን ለማፍራት ቁርጠኛ ሆና እየሰራች እንዳለች ተጫዋቿ ትጥቁን ባበረከተችበት ወቅት ተናግራለች።


አስተያየት ይስጡ