ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም በግዜው አለመከፈል ምክንያት ከሲዳማው ጨዋታ መልስ ልምምድ ያቆሙት የጣናው ሞገድ ተጫዋቾች ትናንት የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ነገ ለሁሉም ተጫዋቾች ደሞዝ እንደሚገባላቸውና ወደ መደበኛ ልምምዳቸውም አንደሚመለሱ የተናገሩ ቢሆንም ተጫዋቾቹ እስካሁን የገባላቸው የአንድ ወር ብቻ መሆኑና በዚህም ተጨዋቾቹ ደስተኛ እንዳልሆኑ እና የሶስት ወር ደሞዝ ካልገባልን ልምምድ አንጀምርም ማለታቸውን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጠናል ።
የፊታችን ቅዳሜ በስምንተኛው ሳምንት ወልዋሎን ሚገጥሙት ባህርዳሮች፤ለቅዳሜው ጨወታ የመጫወታቸው ነገር በሚቀጥሉት ሰዓታት ከክለቡ ፕሬዝዳንትና ከከተማዋ ምክትል ከንቲባ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ሚታወቅ ይሆናል።