በሀያ አምስተኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ሶስተኛ ዕለት ጨዋታ የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት ደምድመዋል።
በጨዋታዉ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰዱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ13ተኛዉ ደቂቃ ላይ በይገኑ ተሾመ ሙከራ ማድረግ የቻሉት ፈረሰኞቹ በ17ተኛዉ ደቂቃ መሪ መሆን የቻሉበትን ግን ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም አማኑኤል ኤረቦ ለበረከት ወልዴ ያቀበለዉን ኳስ ተጫዋቹ ወደ ግብነት መቀየር ይሏል።
ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ለመንቀሳቀስ የጀመሩት ሀድያዎች በመጀመሪያው አጋማሽ በተመስገን ብርሐኑ እና ፀጋዓብ ግዛዉ አማካኝነት በ24ተኛዉ እና 30ኛዉ ደቂቃ ላይ ሁለት ሶስት ተጠቃሽ ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ማርቆጠር ሳይችሉ አጋማሹ በፈረሸኞቹ መሪነት ተገባዷል።
- ማሰታውቂያ -
ከዕረፍት መልስ ሁለት ተጫዋቾችን ቀይሮ ወደ ሜዳ ያስገባዉ ሀድያ ሆሳዕና በ65ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ለማስቆጠር ተቃርቦ ነበር ፤ በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል በረከት ወ/ዮሐንስ ያሻገረዉን ኳስ ተስገን ብርሀኑ በጭንቅላቱ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ወጥታለች።
በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ ተቀይሮ የገባዉ በየነ ባንጃዉ ያቀበለዉን ኳስ ሳሙኤል ዮሐንስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የግቡ ቋሚ ከመለሰዉ በኋላ ኳሷን ያገኘዉ ዑመድ ዑክሪ ወደ ግብነት ቀይሯል። በቀሪ ጨዋታዎች ሁለቱም ክለቦች ተመጣጣኝ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ አድርገዉ ጨዋታቸዉን አንድ አቻ አጠናቀዋል።
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ መቻል ሀዋሳ ከተማን በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።
ምሽት 12:00 ሰዓት ሲል በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ መሪነት በጀመረዉ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ላይ በተመጣጣኝ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ መርሐግብራቸዉን የጀመሩ ሲሆን ፤ አጀማራቸዉ የተሻለ የነበሩት መቻሎም ቀዳሚ ሙከራ ማድረግ ችለዋል። በዚህም በ5ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር በኩል ሽመልስ በቀለ ያሻገረለትን ኳስ ከንዓን ማርክነህ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ግን ለጥቂት በግቡ ቋሚ አጠገብ ወጥታለች።
በአብዝኛዉ ደቂቃ ጨዋታዉን ለመቆጣጠር የተቸገሩት ሀይቆቹ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በ14ተኛዉ ደቂቃ ላይ መቻልች በራሳቸዉ የሜዳ ክፍል ላይ በኳስ ቅብብል ወቅት የሰሩትን የቅብብል ስህተት ተከትሎ ኳሱን ያገኘዉ አጥቂዉ አሊ ሱለይማን ከሳጥን ውጭ አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ሲችል ለራሱም አስራ አተኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።
በ25ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር በኩል ሽመልስ በቀለ ያሻማዉን ኳስ ተከላካዮች ሲመልሱት ያገኘዉ ከንዓን ኳሷን ሲጨርፋት ያገኛት ምንይሉ ወንድሙ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ አዉጥቷታል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ የአቻነት ግብ ፍለጋ መታተር የቀጠሉት መቻሎች ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በ35ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከኋላ ክፍል የተሻገረዉን ኳስ የተቆጣጠረው ሽመልስ በቀለ አጠገቡ ለሚገኘዉ ከንዓን ማርክነህ አቀብሎት ተጫዋቹም ከሀዋሳ ከተማ ተከላካዮች ጋር ታግሎ ኳስ የቻርልስ ሉክዋጎ መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ አጋማሹ ሊጠናቀቅ ሶስት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ሀይቆቹ ሶስተኛ ግብ በአሊ ሱለይማን አማካኝነት ለማስቆጠር ተቃርበዉ የነበረ ቢሆንም የግቡ ቋሚ ግን ከልክሏቸዉ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከዕረፍት መልስ በ59ነኛዉ ደቂቃ ላይ አሊ ሱለይማን ላይ የቻሉ ተከላካይ ነስረዲን ሀይሉ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አሊ ሱለይማን ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን ዳጎሚ መሪ ማድረግ ችሏል።
የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት መቻሎች በ69ነኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል የተሻገረዉን ኳስ ተከላካዮች ተደርበዉ ሲመልሱት በቅርብ ርቀት ኳሷን ከሳጥን ውጭ ያገኘዉ ከንዓን በቀጥታ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።
ወደ ቀኝ መስመር በኩል ጨና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት መቻልች በ79ነኛዉ ደቂቃ ላይ ሶስተኛ ግብ ማግኘት ችለዋል ። በዚህም በተጠቀሰዉ ደቂቃ ከቀኝ መስመር ሳሙኤል ሳሊሶ ያሻማዉን ኳስ ተከላካዮች በሚገባ ማፅዳት ባለመቻላቸዉ ምክንያት ኳሷን አየር ላይ ያገናኛት አብዱ ሞታላቦ በመቀስ ምት ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ወደ መሪነት ማምጣት ችሏል።
በቀሪ ደቂቃዎች በሁለቱም ክለቦች በኩል አዝናኝ የሜዳ ላይ ፉከክር አስመልክተዉን ጨዋታዉ በመቻል 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።