የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምዳቸውን ቀጥለዋል !

 

ዋልያዎቹ ከፊታችን ለሚጠብቃቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ ኒጀር ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ጠንከር ያለ ልምምዳቸውን ማደረግ ቀጥለዋል ።

ዛሬ ረፋድ 3:12 ሲል በጀመረው የልምምድ መርሐ ግብር ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከቡድን ስብስብ ውጪ ከሆኑ ተጫዋች ውጪ ልምምዳቸውን ማድረግ ችለዋል ።

በዛሬው ልምምድ ላይ የፊት መስመር አጥቂው አቡበክር ነስሩ ልምምድ መስራት መጀመሩን ለመመልከት ስንችል በዛምቢያው የሁለተኛ ጨዋታ ተቀይሮ መግባት የቻለው አማኑኤል ዮሐንስ ቀለል ያለ ልምምዶችን ከዋናው ቡድን ተለይተው ሲያሟሙቅ ታይቷል ።

 

በዛሬው ልምምድ መሐል ላይ ቀደም ብለን ወደ እናንተ ለማድረስ እንደሞከርነው ሙጂብ ቃሲም ጉዳት ሲያስተናግድ ልምምድ ለማቋረጥ ተገዷል ። መጠነኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ በወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ያልቻለው አቡበከር ነስሩ በመጪው ቀናት ሙሉ ለሙሉ በማገገም ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ይጠበቃል ።

በዛሬው ልምምድ ላይ ተጫዋቾቹ ተከፋፍለው የተለያዩ የእርስ በእርስ ግጥሚያዎችን ሲያደርጉ 5:00 ሰዓት ላይ የረፋድ ልምምዳቸውን አገባደዋል ።


 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor