ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ዛሬ 10 ስአት ላይ የሚካሄደውን የኤስፒራንስ ዲ ቱኒዝና ኤቷህል ዶ ሳህል ጨዋታ ይመሩታል።
የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዲመደቡለት የጠየቀው ጥያቄ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዘንድ ተቀባይነት አግንቶ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ እንደሚመሩ መደረጉን የወጡት መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ።በአፍሪካ እግር ኳስ በጠንካራ ተፎካካሪነታቸው ከሚጠቀሱት ክለቦች መካከል የቱኒዚያው ኢስፔራንስ ዲቱኒዝ እና ኤቷል ዶሳሂል የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ፌደሬሽኑ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባአምላክ ተሰማ እና ሁለት ረዳት ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመድብላቸው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በላኩት የትብብር ደብዳቤ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን። ጥያቄው ተቀባይነት አግንቶ በዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ይህንን ጨዋታ ሲመሩት 1ኛ ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤለ 2ኛ ረዳት ዳኛ ከግብፅ 4ኛ ዳኛ ለሚ ንጉሴ መሆናቸው ተረጋግጧል ። ዋና ዳኛው አምና በአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ በሩብ ፍፃሜ ውጥረት ውስጥ የነበረው የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ በብቃት መወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከባአምላክ በተጨማሪ የደቡብ አፍሪካው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቪክቶር ጎሜዝ ጨዋታውን እንዲመሩ ጥሪ ቢደረግላቸውም የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውድቅ አድርጓል።