*…በናይሮቢ ለኬንያ ኢንስትራክተሮች ስልጠና
ሰጥተዋል…
የፊፋ ቴክኒካል ኤክስፐርትና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለኬኔያ ኢንስትራክተሮች የሰጡትን ስልጠና ጨርሰው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
የኬንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ15 የሀገሪቱ ኢንስትራክተሮች ስልጠና እንዲሰጥላቸው ለካፍ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ካፍ የፊፋ ቴክኒካል ኤክስፐርትና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር የሆኑትን አብርሃም መብራቱን ወደ ናይሮቢ በመላክ ስልጠናውን እንዲሰጡ ማድረጉ ታውቋል።
ኢንስትራክተር አብርሃምም ባለፉት 12 ቀናት ሁለት ሴት ኢንስትራክተሮችን ጨምሮ ለ15 የኬንያ ኢንስትራክተሮች ስልጠናውን ሰጥተው ተመልሰዋል።