መነሻ ገጽ Betaking Ethiopia Primer League ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 12ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
Betaking Ethiopia Primer Leagueቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 12ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

አጋራ
አጋራ

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 12ኛ ሳምንት በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አምስት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 8 ጎሎች በ8 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አንድ በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 25 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ታህሳስ 7 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች ምንይሉ ወንድሙ(መቻል) በ12ኛ ሳምንት ጨዋታ ከጨዋታ በኋላ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀርበበት ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

ባህርዳር ከተማ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ የባህርዳር ከተማ ቡድን አምስት በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

በክለቦች ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው የ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች የዕለቱን ዋና ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት በመቅረቡ ደጋፊዎቹ በዕለቱና ከዚህ በፊት ተሳድበው በተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር ሰባ አምስት ሺሕ /75 000/ እንዲከፍል ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...