የጨዋታ ዘገባ | አፄዎቹ ወደ ድል ተመልሰዋል

 

ዛሬ ረፋድ ካይ በተካሄደው እና በፋሲል ከተማ የበላይነት በተጠናቀቀው ጨዋታ አፄዎቹ በሽመክት ጉግስ ድንቅ ብቃት ታግዘው ወደ አሸናፊነት የተመለሱበትን የጨዋታ ውጤት ይዘው ወጥተዋል ።

ተቀዛቅዞ በጀመረው የጨዋታ ሂደት ፋሲል ከተማዎች የኳስ ብልጫን ይዘው በተቃራኒው ጅማ አባ ጅፋሮችን መከላከል አማራጫቸው አድርገው የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ደቂቃዎች ዘልቀዋል ። የመጀመሪያ አስደንቃጋጭ ሙከራቸውን ለማድረግ ሀያ አራት ደቂቃዎችን የጠበቁት አፄዎች በያሬድ ባየህ ጥሩ የግንባር ኳስ ሙከራ ቢያደርጉም የግቡን የላይኛውን አግዳሚ ታካ ወጥታለች ። ከዚህ እንቅስቃሴ በኋላ ወደ ግብ ቶሎ ቶሎ መቅረብ የቻሉት አፄዎቹ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በ ሙጂብ ቃሲም እና በአምበላቸው ያሬድ ባየህ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለው ነበር ።

ተደጋጋሚ ሙከራዎቻቸው ፍሬ ያፈራላቸው ፋሲል ከተማዎች በእለቱ ልዩ የነበረው ሽመክት ጉግሳ ላይ የተሰራውን ጥፋት አምሳሉ ጥላሁን ከሳጥን ውጪ ያገኘውን ቅጣት ምት ወደ ግብነት በመቀየር ፋሲል ከተማዎችን መሪ አድርጓል ። ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ ፋሲል ከተማዎች ጥሩ አጋጣሚን ሲያገኙ ከመሀል ሜዳ ሱራፌል ዳኛቸው በግሩም ሁኔታ ያሾለከውን ኳስ ሽመክት ጉግሳ ለ ሙጂብ አመቻችቶ በማቀበል የአፄዎቹን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል ።

የመጀመሪያ አጋማሽ በዚሁ ሲጠናቀቅ በሁለተኛው አጋማሽ ጅማ አባ ጅፋሮች ከመጀመሪያ የጨዋታ አጋማሽ ተሽለው ሲገኙ ግብ ማስቆጠርም ችለዋል ። ጅማ አባ ጅፋሮች የ ፋሲል ከተማውን ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኪ መዘናጋት ተከትሎ በ ብዙአየሁ እንዳሻው አማካኝነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። ከግቡ መቆጠር በኋላ ዳግም ወደ ኋላ የፈገፈጉት ጅማ አባ ጅፋሪችን ግብ ለማስተናገድ ሲገደዱ ሽመክት ጉግሳ በተከላካዮች መሀል በግሩም ሁኔታ ያሾለከለትን ኳስ አዲስ ፈራሚው ሳሙኤል ዮሐንስ የአፄዎቹን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ለማድረግ ችሏል ።

የጨዋታው መገባደጃ እየተቃረበ ሲሄድ በዕለቱ ልዩ የነበረው ሽመክት ጉግሳ ከ በረከት ደስታ ጋር በመቀባበል የአፄዎቹን አሸናፊነት ያበሰረች ግብ ከመረብ በማሳረፍ ጨዋታው በፋሲል ከተማ የበላይነት ሊጠናቀቅ ችሏል ።

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከተማ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ሲሉ በተቃራኒው ጅማ አባ ጅፋሮች አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor