በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ከ ኢትዮጵያ ቡና ነገ 09:00 ሰዓት ጨዋታቸውን እሚያደርጉ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ቡናዎች ትናንት አዲግራት ሲገቡ በህዝቡ መልካም አቀባበል ታጅበው ካረፉበት ሙሉ ሆቴል ወደ ወልዋሎ ስታድየም በማምራት የመጀመርያ ቀን ትሬኒጋቸውን 10:00 ሰአት ላይ መስራት ችለዋል፡፡
አመሻሹ ላይም በ ገዛገብረስላሴ ባህላዊ የምግብ አደራሽ የእንኳን ደህና መጣቹና የእራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ቡናዎቹ ዛሬ ጠዋት ላይ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅበው የሁለተኛ ቀን ትሬኒንግ ሲሰሩ ዋና አሰልጣኛቸው ኮስታዲን ፓፒች በቦታው ላይ አልነበሩም በምትካቸው ምክትል አሰልጣኙ እና ኮቺንግ ስታፍ በሙሉ በትሬኒንግ ቦታው ላይ ተገኝተው ተጫዋቾቹን ልምምድ አሰርተዋል፡፡
በነገው ጨዋታ ከሁለቱም ቡድኖች በጨዋታው ላይ እማይኖሩትን ስንመለከት ቡናዎቹ ከወልዋሎ ያስፈረሙት አብዱሰላም አማን በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ጋር ያልተጓዘ ሲሆን ለብሔራዊ ቡድኑ ያስመረጧቸው ሳምሶን ጥላሁን እና በጉዳት ምክኒያት የተቀነሰው መስዑድ መሀመድ እና አስቻለው ግርማ እማይኖሩ ሲሆን የወልዋሎ አዲግራት ግብ ጠባቂ በረከት አማረ በተመሳሳይ የብሔራዊ ቡድን ግዴታውን ለመወጣት ለቢጫዎቹ እማይሰለፍ ይሆናል፡፡