መነሻ ገጽ መከላከያ የጨዋታ ዘገባ | ፋሲል ከነማ መከላከያን በመርታት መሪነቱን አጠናክሯል
መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | ፋሲል ከነማ መከላከያን በመርታት መሪነቱን አጠናክሯል

አጋራ
አጋራ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በፋሲል ከተማ እና መከላከያ መካከል በተደረገ ጨዋታ ተጀምሯል ። በጨዋታው ብልጫ የነበራቸው አፄዎቹ ያሬድ ባየህ ከእረፍት መልስ 49ኛ ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 1 ለ 0 አሸንፈው መሪነታቸውን አጠናክረዋል ።

ፋሲል ከተማዎች ከባህርዳር ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የነበረውን ቋሚ 11 ምንም ሳይለውጡ የገቡ ሲሆን በመከላከያ በኩል ከሲዳማ ቡና አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ልደቱ ጌታቸውን እና ዳዊት ወርቁን ቀይረው በማስገባት ጨዋታውን ጀምረዋል ።

በጨዋታው ጅማሮ መከላከያ ረጃጅም ኳሶችን ወደ ፊት በመላክ ዕድሎች ለመፍጠር የሞከሩበት ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ግን ጨዋታው በፋሲል ከተማ የበላይነት ተካሂዷል ። በጨዋታው የመጀመሪያ ሙከራ መከላከያዎች ግብ ሊያስቆጥሩ የሚችልበትን ትልቅ ዕድል በአቤል ነጋሽ አማካኝነት ቢያገኙም ሊጠቀሙበት አልቻሉም ። ሳማኪ ለቡድን አጋሩ በእጁ ለመወርወር ሲሞክር በመሳሳቱ ኳሱን ያገኘው አቤል ኳሱነን ወዲያው ወደ ግብ ቢሞክረውም ሳማኪ እንደምንም አውጥቶታል ።

አፄዎቹ የኳስ ቁጥጥሩን ብልጫ በመውሰድ በተለይም ከመስመር ወደ ግብ በሚሻገሩ ኳሶች ተደጋጋሚ ጥረቶችን ማድረግ ችለዋል ። 5ኛው ደቂቃ ላይ አምሳሉ ጥላሁን ከግራ መስመር ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ኦኪኪ በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ሙከራ ለጥቂት ወቶበታል ።

የፋሲል ከተማ አብዛኛው የማጥቃት እንቅስቃሴ ከግራ መስመር የተነሳ ሲሆን ከውሀ እረፍት በኋላ ግን በቀኝ መስመርም ተመሳሳይ ሁነቶችን ተመልክተናል ። መከላከያዎች በተወሰደባቸው ብልጫ በራሳቸው ሜዳ ተወስነው ለመቆየች የተገደዱ ሲሆን በ39ኛው ደቂቃ ላይ ሌላ የግብ ዕድል ማግኘት ችለው ነበር ። ያሬድ ባየህ ለማቀበል ያደረገው ጥረት በቢንያም በላይ ሲመለስ ኳሱን ያገኘው አቤል ነጋሽ ጥቂት ጠጋ ብሎ አክርሮ የመታው ኳስ በሚካኤል ሳማኪ በድጋሚ ተመልሷል ።

የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ በተጨመሩት ሶስት ደቂቃዎች ላይ ሽመክት ወደ ግብ ክልል ያሻገረውን ኳስ ኢብራሂም ሁሴን አግኝቶ ለማውጣት ሲሞክር በእጁ ኳስ መንካትን ተከትሎ የፋሲል ከተማ ተጫዋቾች በሳጥን ውስጥ ነው የተነካው ብለው ጥያቄ ቢያቀርቡም የዕለቱ የመሀል ዳኛ ሊድያ ታፈሰ ከሳጥን ውጪ ነው የተነካው በማለት የቅጣት ምት ሰጥታለች ።

ሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ በጨዋታው ግብ ተቆጠረ ። አለምብርሀን ይግዛው ከቀኝ መስመር ወደ ግብ የላከው ኳስ የቢንያም ላንቃሞን እጅ በመንካቱ አፄዎቹ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት አምበሉ ያሬድ ባየህ አስቆጥረ ።

 

ከግቡ መቆጠር በኋላ መከላከያዎች መነቃቃትን ማሳየት የቻሉ ሲሆን ቀደም ብሎ ከነበረው የተሻለ በመንቀሳቀስ የግብ ዕደሎችን ለመፍጠር ጥሰቶችን ያደረጉበት ነበር ። ነገር ግን በተደጋጋሚ ያገኟቸውን የማዕዘን ምቶች መጠቀም አለመቻልና ከግብ ጠባቂው በረጅሙ የሚላኩ አድራሻቸው የማይታወቅ ኳሶች ቡድኑን ዋጋ አስከፍለውታል ማለት ይቻላል ። አፄዎቹ የሚያገኟቸውን ኳሶች በፍጥነት ወደ ፊት በማድረስ ተጨማሪ ግቦችን ለማግኘት ያደረጓቸው ጥረቶች በመከላከያ ተከላካዮች ሊመክኑ ችለዋል ።

48ኛ ደቂቃ ላይ ሽመክት ጉግሳ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ በቀላሉ በክሌመንት ቦዬ ተይዞበታል ። 61ኛው ደቂቃ ላይ ኦኪኪ አፎላቢ ተቀይሮ ከገባው ሳሙኤል ዮሀንስ ከቀኝ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንቦት ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት በግብ ጠባቂው የዳነተበት ሲሆን በ77ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ሳሙኤል ዮሀንስ ከይሁን እንደሻው ጋር ባደረገው ቅብብል በሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ በተከላካዮች ተመልሶበታል ። በቀሪዎቹ ደቂቃዎች መከላከያዎች ወደ አፄዎቹ የሜዳ ክፍል በመግባት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ያደረጓቸው ጥረቶች ውጤታማ ሳይሆኑ ጨዋታው ፍፃሜወን አግኝቷል ።

ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከተማ ነጥቡን 17 በማድረስ መሪነቱን ሳያጠናክር መከላከያ በበኩሉ በ11 ነጥብ ባለበት 10ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...