በዛሬዉ እለት ወደ ዝዉዉሩ ገበያ በመግባት አማኑኤል ኤርቦን ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ያስፈረሙት ፈረሰኞቹ የአምስት ተጫዋቾችን ኮንትራት ማደሳቸዉን ይፋ አድርገዋል።
ተጫዋቾቹ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ከተስፋ ቡድን ያደጉትን ዳግማዊ አርአያ ፤አብርሀም ጌታቸው ፣ተገኑ ተሾመ ፣አላዛር ሳሙኤል ፣ሻሂድ ሙስጠፋ ዉላቸዉን በማራዘም የሁለት አመት ኮንትራትም ፈርመዋል።
በቀጣይም ቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ጨምሮ ሌሎች ዝዉዉሮችን እንደሚፈፅም ይጠበቃል።