በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የግብጹ አልአህሊና የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ካይሮ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ በኢትዮጲያዊያን ዳኞች እንደሚመራ ታውቋል።
ካፍ ቅዳሜ ለሚካሄደው ለዚህ ትልቅ ጨዋታ የመሃል ዳኝነቱን ለአርቢትር በዓምላክ ተሰማ ሰጥቷል። ረዳት ዳኝነቱን ትግል ግዛውና ተመስገን ሳሙኤል ሲመሩት ለአራተኛነቱ ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ መመደቡ ካፍ አሳውቋል።
ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር የማማሎዲ ሰንዳውንስ ተጨዋች ሲሆን ከጉዳቱ ባለማገገሙ መካፈል አለመካፈል አልተረጋገጠም።