መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና አንጋፋዉ የመስመር ተከላካይ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሏል!!
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

አንጋፋዉ የመስመር ተከላካይ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሏል!!

አጋራ
አጋራ

በዘንድሮዉ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለዋንጫ ሲፎካከሩ ቆይተዉ በሁለተኝነት ደረጃ ሊጉን ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ቡናዎች ለቀጣዩ አመት ለሚኖራቸው ዉድድር በተለይም ከረዥም ጊዜ በኋላ በተመለሱበት የአፍሪካ መድረክ ላይ ጥሩ ተፎካካሪ ሁነዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በመቀላቀል እና የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ ይገኛሉ።

በ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን ከመቐለ 70 አንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለዉን የመስመር ተከላካይ ስዩም ተስፋየ በአንድ አመት የኮንትራት ጊዜ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሏል።

ከዚህ ቀደም በመተሐራ፣ በኒያላ፣ በመብራት ፣በደደቢት፣በመቐለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለዉ ስዩም
በትግራይ ክልል በነበረው ችግር ምክንያት መቀለ 70 እንደርታ በሊጉ መሳተፍ ባለመቻሉ የዘንድሮዉ የዉድድር አመት ላይ ወደ ወልቂጤ ከተማ ማምራት ችሎ የነበረ ሲሆን፤ በሲዝኑ ግማሽ ላይ ግን ላለመዉረድ ሲታገል ወደ ነበረዉ ጅማ አባጅፋር በመዛወር ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ ችሎም ነበር።

ተከላካዩ ስዩም ተስፋየ ለረጅም ዓመታት በብሄራዊ ቡድን እና በክለብ ደረጃ በመጨወትም የሚታወቅ ተጨዋች ሲሆን በአፍሪካ መድረክ ለሚሳተፉት ኢትዮጵያ ቡናዎችም ተጨማሪ ጥንካሬን እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...