ፋሲል ከነማ በ2014 የዉድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛል።
እስካሁን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ የቀላቀሉት ፋሲል ከነማዎች በዛሬው ዕለት የተከላካዩ ዳንኤል ዘመዴን እና የተከላካይ አማካኙን የኪሩቤል ኃይሉን ውል ለተጨማሪ አመት አራዝመዋል፡፡
ከፋሲል ከነማ ታዳጊ ቡድን የተገኘዉ ወጣቱ ተከላካይ ዳንኤል ዘመዴ ምንም እንኳን በቋሚ አሰላለፍ ዉስጥ ገብቶ መጫወት ባይችልም ከክለቡ ጋር ለቀጣይ አመታት ለመቆየት ተስማምቷል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ፍሬ የሆነው የተከላካይ አማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ኪሩቤል ሀይሉ እንደ ዳንኤል ሁሉ ዘንድሮ በክለቡ ብዙም የመሰለፍ ዕድል እያገኘ ባይሆንም ከሻምፒዮኖቹ ጋር ለተጨማሪ አመት የሚያቆየውን ዉል ፈርሟል።
አስተያየት ይስጡ