የፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የ ሴካፋ ከ 23 ዓመት በታች ውድድር የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ይፋ ሆኗል ።
ዘጠኝ ሀገራትን ተሳታፊ የሚያደርገው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ በትናንትናው ዕለት መከናወኑ ይታወቃል።
ከደቂቃዎች በፊት በወጣ መረጃ መሰረት ውድድሩን የማስተላለፍ መብት ያለው የታንዛኒያው አዛም የቴሌቪዥን ጣቢያ ሙሉ ውድድሩን እንደሚያስተላልፍ ይፋ ሆኗል ።
በተያያዘም አማራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨዋታዎች ለማስተላለፍ ፍላጎት ያለዉ ሲሆን ፤ ዉድድሩን የማስተላለፍ ሙሉ ፍቃድ ላለዉ አዛም ቴሌቪዥን ጥያቄዉን አቅርቦ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።