ለምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ23 ዓመት በታች ውድድር በዛሬው እለት(ሐምሌ 7/2013) ወደ ባህር ዳር ለተጓዘው የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ተደረገለት።
ቡድኑ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥ/አ ኮሚቴ አባል እና የሴካፋ ብሔራዊ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ እንዲሁም የተለያዩ የኮሚቴው አባላት አቀባበል አድርገው ወደ ሚያርፍበት ሆቴል አጅበው በማድርስ የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
© Ethiopian Football Federation