በዉድድር አመቱ በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ባልተጠበቀ መልኩ በወራጅ ቀጠናዉ ላይ ለወራት ያክል ላለመዉረድ ሲፎካከር የነበረዉ ሲዳማ ቡና በዉድድሩ አመቱ አጋማሽ ላይ የቀድሞዉን አሰልጣኙን ዘርዓይ ሙሉ በማሰናበት መቀሌ 70 እንደርታ በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ አለመሳተፉን ተከትሎ ያለ ክለብ የቆዩትን አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር በሊጉ ለመቆየት ችሏል።
አሁን ደግሞ ይበልጥ ራሱን ለማጠናከር በዝዉዉር መስኩቱ ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ተሳታፊ ከሆነዉ ኮልፌ ቀራኒዮ የመስመር አጥቂ ተጫዋቾቹን ብሩክ ሙሉጌታ እና አንዋር ዱላ በዛሬዉ ዕለት ማስፈረማቸዉን ይፋ አድርገዋል።
የትግራይ ክልል ክለቦች በቀጣይ አመት በሊጉ የማይሳተፉ ከሆነ እነርሱን ለመተካት በሚል በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተዘጋጀው ዉድድር ላይ ጥሩ ብቃትን ማሳየት የቻሉት ሁለቱ ተጫዋቾች ምንም እንኳን ክለባቸዉ ኮልፌ ቀራኒዮ በቀጣይ አመት በሊጉ የሚያሳትፈውን ደረጃ መያዝ ባይቻልም በአዲሱ የዉድድር አመት ተጫዋቾቹን በአዲስ ክለብ የምንመለከታቸዉ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ