የኤርትራን የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ23 ዓመት በታች ውድድር በዛሬው እለት (ሐምሌ 7/2013) ማምሻውን ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል ።
ልዑካኑ ከምሽት 2:30 ባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል ።
ኬንያን ተከትለው በትናትናው እለት የገቡትን የአባል አገራት ቡድኖች የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣ የሚመሩት ካቢኔ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥ/አ ኮሚቴ አባል እና የሴካፋ ብሔራዊ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ዋና ፀሐፊ እና የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ሰለሞን ገ/ሥላሴ ጨምሮ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴዎች አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በኦሊቨ ሆቴል እንዲሁ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በአባይ ምንጭ ሆቴል ማረፊያቸውን አድርገዋል።
- ማሰታውቂያ -
©EFF