የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከነገው ተጠባቂ ጨዋታ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በZoom ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምን አሉ ?
” መጠነኛ ጉዳት የነበረባቸው ተጫዋቾች ሙሉ ለ ሙሉ አሁን ላይ ጤነኛ እንደሆኑ የጋና ብሄራዊ ቡድን ጠንካራ ነው ፣ የተወሰኑ የ ጨዋታ ቪድዮዎችን ለመመልከት ችለናል። በተጨማሪም የቀደመ ውጤት እያሰብን ከተጫወትን ከባድ ነው ፣ ብሄራዊ ቡድችን ከ ጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እየመጣ ነው። ከኮቪድ መልስ ከዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ካደረግነው የወዳጅነት ጨዋታ ጀምሮ እስከ አሁን ካየነው ቡድናችን እድገት እና ለዉጥ አለው። መልካም ነገርም ይገጥመናል ብዬ ነው የማስበው ” በማለት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በተጨማሪም አሰልጣኙ ከዋልያዎቹ የስለተቀነሱት አራት ተጫዋቾች?
” ብሄራዊ ቡድኑን በተቀላቀሉ ጊዜ አብረን በምንቆይባቸው ጊዜያት ሊያደርጉ የሚገባቸውን እና ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች የተቀመጡ አሉ ። ያለንበት ባህር ዳር የሰዓት ገደብ የተጣለበት ነው አራቱ ተጫዋቾች ስለ ዩጋንዳ ጨዋታ ልናወራቸው ስንፈልጋቸው በክፍላቸው አላገኘናቸውም። ከፍፁም አለሙ ውጪ ያሉት ተጫዋቾች 4:30 ሰዓት ገዳማ ነው የገቡት ከተቀመጠው ገደብ ውጪ ነው ፣ ብሄራዊ ቡድኑም ወዲያውኑ እንዲሰናበቱ አድርገናል።
ከዚያም የአሰልጣኝ ክፍሉን እና ተጫዋቾቹን ይቅርታ መጠየቅ አለብን ብለው ከ አራቱ ተጫዋቾች ጋር ተገናኝተን አውርተን ጥፋታቸውን ራሳቸው አምነው ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ እንዳይገቡ መክረን ተለያይተናል ” ሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተጫዋቾቹ ስለተቀነሱበት ምክንያት ለጋዜጠኞች አብራርተዋል።
በተያያዘም ጋና ለካፍ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ የዋልያዎቹ እና የጋና ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በደጋፊዎች ፊት እንደሚደረግ ታዉቋል። የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በነገው ዕለት ከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ሲል የሚደረግ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ