መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ “በአሰልጣኝነት ታሪኬ ክለብ ስቀይር አንዱን አፍርሼ ሌላውን የገነባሁበት ታሪክ የለኝም”የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

“በአሰልጣኝነት ታሪኬ ክለብ ስቀይር አንዱን አፍርሼ ሌላውን የገነባሁበት ታሪክ የለኝም”የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ

አጋራ
አጋራ

“በአሰልጣኝነት ታሪኬ ክለብ ስቀይር አንዱን አፍርሼ ሌላውን የገነባሁበት ታሪክ የለኝም”

“ብሄራዊ ቡድኑ መገለጫ የሆነ የጌም ሞዴል አልነበረውም አልኩ እንጂ አሰልጣኞቹ የራሳቸው አልነበራቸውም አላልኩም”

የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ

” ከአለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ከመናፍ አወል ጉዳትና ከሽመክት ጉግሳ በቤተሰብ ምክንያት በቡድናችን መለየት ውጪ የተለየ ችግር አልገጠመንም” በማለት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ።

አሰልጣኙ በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በሰጡት መግለጫ” ጋናኘን ከገጠምንበት ጨዋታ በላይ ዚምቧብዌ ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል። በተለይ በሁለተኛ ስቴፕ ኳሷን በነሱ የግብ ክልል ጋር አድርገን የመጫወት ዕድል ፈጥረናል ይሄም ለውጥ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ከዚምቧብዌ ጋር ስለነበረው ጨዋታ የመለሱት አሰልጣኙ “ተከላካዩ አስቻለሁ ታመነ በሁለት ቢጫ መሠለፍ እንደማይችል ባለቀ ሰአት ፊፋ በመግለጹ መግባት አልቻልንም በቦታው ተተኪው የነበረው መናፍ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ማገገም ባለመቻሉ ቦታው ላይ ልምድ የሌለውን አህመድ ረሺድን ለመጠቀም ተገደናል ያም ሆኖ ፊፋ እንደገና በላከው ደብዳቤ አስቻለሁ መሰለፍ ይችላል ደብዳቤው ስህተት ነው ቢልም ሰአቱ ደርሶ ስለነበር ከተቀያሪነት ውጪ መጠቀም አልቻልንም” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

ስለ አቡበከር ናስርና ጌታነህ ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኙ” ምንም ጥያቄ የለም በዚህ ሰአት ዋና ተመራጩ ጌታነህ ነው ከሜዳ ውጪና በሜዳ ውስጥ ቡድኑን በሚገባ እየጠቀመና ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው አቡበከርን በተመለከተ ከተጫወተበት ጊዜ ይልቅ ከፊቱ የሚጠብቀው ጊዜ ይበልጣል በቀጣይም የርሱ የሆነ ጊዜ ይኖረዋል” በማለት መልሰዋል።

አሰልጣኙ አሁንም ሊጉን ስለሚያስተናግደው የሃዋሳ ስታዲየም ከመናገር አልተመለሱም..”የቴሌቭዥን ስርጭት ባላቸው ስታዲየሞች ይህን አይነት ሜዳ አላየሁም አግብተው ለጭፈራ ይወድቃሉ ዳይቭም አድርገው ሲነሱ ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም የኛ ሜዳ ግን ተጨዋቾቻችንን እየጎዳቸው ነውና መስተካከል አለበት”ሲሉ አቋማቸውን እንዳልቀየሩ የሚገልጽ ምላሽ ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ ውበቱ አባተ “ለአፍሪካ ዋንጫው ሊጉ የሚዘጋልንና የመዘጋጃ ቀን የሚሰጠን ወደ 12 ቀን ቢሆን ነው ጊዜው ቢያጥርም ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት በምንፈልገው ደረጃ ለመዘጋጀት እንሞክራለን ከውድድሩ በፊትም ወደ 3 የሚጠጉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ለማድረግም አቅደናል” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለ ቡድኑ ጌም ፕላን የተጠየቁት አሰልጣኙ “ይሄ የጨዋታ መንገድ የብሄራዊ ቡድኑ መገለጫ ነው ተብሎ የተቀመጠ የጌም ሞዴል የለንም ስመጣም አላገኘሁም ስንመጣም የጌም ሞዴል እንዲኖረው እንሰራለን ያልኩት ለዚህ ነው ከዚያ ውጪ በሃላፊነት ላይ የነበሩ አሰልጣኞቹ ጌም ሞዴል አልነበራቸውም አላልኩም ይሄ መስተካከል አለበት” ሲሉም በአጽንኦት አሳስበዋል።

” ክለብ ስትቀይር ከወጣህበት ቡድን ብዛት ያለው ተጨዋቾች ትወስዳለህ? ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለብሄራዊ ቡድኑ መጠቀም አትወድም ዝግጁም አይደለህም ወይ? የተባለው አሰልጣኝ ውበቱ “የኔ የአሰልጣኝነት ታሪክ ሲታይ ቡድን አፍርሼ ወደ ሌላ ክለብ የወሰድኩት የለም አቅም ኖሮት ብወስድ ችግር የለውም ጥሩ ከሆኑ ከአንድ ቡድን ሁሉንም ብመርጥ ችግር የለውም መጠየቅ ካለበት ሜዳ ላይ ባለው ውጤት ነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆነው ብቃት ካላቸው በሬ ክፍት ነው የህጋዊነት ጥያቄ መነሳቱም አይቀርም መንግስት ይፈቅዳል ወይ? ለኛ ለመጫወት የያዘውን የጀርመንና የእንግሊዝ ፓስፖርት ቀድዶ ለመምጣት የሚፈቅድ አለ ወይ የሚለው ራሱ ምላሽ ያስፈልገዋል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...