16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ስነስርዓት የፊታችን ህዳር 30/2014 በማርዮት ሆቴል እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሰጠው ውሳኔ መሠረት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ክለቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች የሚገኙበት የማርዮት ሆቴል መርሃግብር በዕለተ ሃሙስ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።
በዕለቱ የውድድሩ ምርጥ 11 ድሪም ቲም ተመርጦ የሚሸለም ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች ኮከብ ለሆኑ በሙሉ ሽልማት የሚበረከትበት መርሃግብር መሆኑ ታውቋል።
16ኛውን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ የሚሰለጥነው ባህርዳር ከተማ ማሸነፉ ይታወቃል።
አስተያየት ይስጡ