መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ የጨዋታ ዘገባ |ዋልያዎቹ የምድባቸዉን የመጨረሻ ጨዋታ በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የጨዋታ ዘገባ |ዋልያዎቹ የምድባቸዉን የመጨረሻ ጨዋታ በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድባቸዉን የመጨረሻ ጨዋታ ከዙምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከሜዳቸው ዉጭ አድርገው አንድ አቻ በሆነ ዉጤት አጠናቀዋል።

በዋልያዎቹ በኩል የምድቡን አምስተኛ ጨዋታቸዉን ሲያደርጉ ከተጠቀሙት ቋሚ 11 ተጫዋቾች መካከል ተከላካዩን አስቻለው ታመነ በአህመድ ረሽድ እንዲሁም አማካዩን መስዑድ መሀመድ በሀይደር ሸረፋ ቀይረዉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

ምንም እንኳን ይህ ነዉ የሚባል የዉጤት ጠቀሜታ ያልነበረው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ለመርሀግብር ሟሟያነት ከመጫወት በዘለለ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ላለማጠናቀቅ በሚመስል መልኩ የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ የተወሰነ የፉክክር መንፈስን አስመልክቶናል።

የጨዋታውን የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ያክል ተመሳሳይ በሚመስል መልኩ ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ኳስን ከኋላ መስርተው ለመዉጣት ተደጋጋሚ ጥረትን ሲያደርጉ የተመለከትን ሲሆን ነገር ግን ከሜዳዉ የመሀል ክፍል አልፈዉ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ የሚያደርጓቸው ሙከራቸዉ በተደጋጋሚ ሲቆራረጡ ተስተውሏል።

በጨዋታውም ጅማሮም በ5ኛዉ ደቂቃ ላይ የዋልያዎቹ የፊት አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከዳዋ ሁቴሳ የተሻገረለትን ኳስ ለአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሽመልስ በቀለ ሲያቀብለዉ ነገር ግን አማካዮ ሽመልስ ሳይጠቀምባት ቀርቷል። በድጋሚ በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ የተገኘዉን የቅጣት ምት ኳስ የመስመር አጥቂው አቡበከር ናስር ወደ ግብ ሲያሻማዉ ተከላካዩ ምኞት ደበበ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም ኢላማውን ሳይጠብቅ ወጥቷል።

በድጋሚ ዳዋ ሁቴሳ በ12ኛዉ ደቂቃ ላይ ጥሩ የግብ ማግባት እድልን ቢያገኝም በረኛዉ ቩላ አዉጥቶበታል። ከስምንት ደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ዳዋ ሁቴሳ ከአማኑኤል የተሻገረለትን ድንቅ ኳስ ወደ ግብነት ለመቀየር ቢሞክርም በተከላካዮች ርብርብ ኳሷን አዉጥተዋታል።

በዋልያዎቹ የተሻለ የጨዋታ የጨዋታ ብልጫ የቀጠለዉ የሁለቱ ሀገራት ጨዋታም በ29ኛዉ ደቂቃ ላይ አስደንጋጭ ሙከራን አስመልክቶናል። በተጠቀሰው ደቂቃም ዙምባቡዌዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት በአምበላቸዉ አማካኝነት ሲያሻሙ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ኢስማኤል ቢሞክርም ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል።

በሂደት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ሲጥሩ የነበሩት ዙምባቡዌዎችም በ39ኛዉ ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ግብ አግኝተዋል። በዋልያዎቹ የተከላካዮች እና ግብ ጠባቂ አለመግባባት የተፈጠረዉን ስህተት ተጠቅሞ በመሀል ሜዳዉ ላይ ይገኝ የነበረዉ ማሀች ከርቀት ግሩም ግብ በማስቆጠር ሀገሩን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላም በዋልያዎቹ በኩል የተለየ አስደንጋጭ ሙከራ ሳያሳየን የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ተሻሽለው የተመለሱት ዋልያዎቹ በ50ኛዉ ደቂቃ ላይ በአንበሉ ጌታነህ ከበደ አማካኝነት ድንቅ የሚባል ሙከራን ቢያደርጉም የግብ አግዳሚዉ መልሶባቸዋል። ከዚች ለግብ የቀረበች ሙከራ በኋላ በተደጋጋሚ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ የአቻነት ግብ ለማግኘት ሲሞክሩ በዋልያዎቹ በኩል የተስተዋለ ሲሆን፤ በአንፃሩ በባለሜዳዎቹ በኩል መሪነታቸውን አስጠብቀዉ ለመዉጣት በሚመስል መልኩ ወደራሳቸው የግብ ክልል በማፈግፈግ በአጋጣሚዎች የሚያገኟቸዉን ኳሶች ክሮስ በማድረግ ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ሲጥሩም ተመልክተናል። ለዚህም እንደማሳያነት በተደጋጋሚ ከግራ መስመር በኩል ረጃጅም ኳሶችን ወደ ዋልያዎቹ የግብ ክልል በመላክ ተከላካዮቹን እና ግብ ጠባቂውን ተክለማርያምን ሲፈትኑ ተስተውሏል።

በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይም የአቻነት ግብ ለማግኘት ታትረዉ ሲሞክሩ የነበሩት ዋልያዎቹ ዉጥናቸዉ ሰምረዉ በ86ኛዉ ደቂቃ ላይ አቻ ሆነዋል። በጨዋታው ተቀይሮ የገባው የመስመር ተጫዋቹ መስፍን ታፈሰ ያቀበለውን ኳስ አጥቂው አቡበከር ናስር ግብ ጠባቂውን በማለፍ ግሩም ግብ አስቆጥሯል። ከግቧ መቆጠር በኋላ ይህ ነዉ የሚባል የተለየ የግብ ሙከራ በሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በኩል ሳይደረግ ጨዋታው ተጠናቋል።

በዚህ መሰረትም ዋልያዎቹ ምንም እንኳን ወደ ቀጣዩ ዙር አለማለፋቸዉን አስቀድመዉ ቢያውቁም የዛሬውን ዉጤት ተከትሎ ምድባቸውን አምስት ነጥብ በመሰብሰብ ሶሰሰተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ የዛሬ ተጋጣሚያቸውን ዙምባቡዌ ደግሞ በሁለት ነጥቦች የምድቡን ግርጌ በመያዝ አጠናቃለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...