መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ዋልያዎቹ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !!
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !!

አጋራ
አጋራ

ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ከቀኑ 1:00 ሰዓት ላይ ከዙምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያካሂዱ ይሆናል።

🇿🇼ዚምባቡዌ ከ ኢትዮጵያ🇪🇹
10:00 ሰዓት

ሁለቱም ሀገራት በምድብ 7 ከ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ጋር ተድልድለዉ ለ2022 የኳታር የአለም ዋንጫ ለማለፍ ዉድድራቸዉን ሲያደርጉ መቆየታቸዉ ይታወቃል። በምድቡ እስከ አሁን ድረስ እያንዳንዳቸው ብሔራዊ ብሔራዊ ቡድኖች አምስት አምስት ጨዋታዎችን አድርገዉ ደቡብ አፍሪካ በ13 ነጥብ ቀዳሚ ስትሆን ጋና በ10 ነጥብ ትከተላለች ዋልያዎቹ በ4 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ የዙምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በሶስት ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል።

አስቀድሞ ወደ መጨረሻው ዙር አለማለፋቸውን ያረጋግጡት ሁለቱ ሀገራትም በዛሬዉ ዕለት በዙምባብዌ ስፖርትስ ስታዲየም የምድባቸውን የመጨረሻ ጨዋታ እንዲሁም የምድቡን ግርጌ ይዞ ላለማጠናቀቅ የሚያደርጉት መርሐ ግብር ይሆናል ።

ሁለቱም ሀገራት ከሶስት ቀናት በፊት የየምድብ አምስተኛ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን የሜዳ ላይ ጨዋታውን ይዞ የተሰደደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ከጋና አቻው ጋር ያደረገዉን ጨዋታ በአንድ አቻ ማጠናቀቁ ይታወሳል።በአንፃሩ የዛሬ ተጋጣሚው ዙምባቡዌ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ 1ለ0 መሸነፋቸው ይታወቃል።

በዛሬዉ ዕለትም የሚደረገው የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ ምንም እንኳን የጨዋታው ዉጤት ያን ያክል የተለየ ተፅዕኖ ባይኖረዉም የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ላለማጠናቀቅ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘም ጨዋታው በፊፋ የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...