መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ የጨዋታ ዘገባ | ዋልያዎቹ እና ጥቋቁር ከዋክብቶቹ በአምበሎቻቸው ግቦች አቻ ተለያይተዋል
ዋልያዎቹዜናዎችየአለም ዋንጫ ማጣሪያጋና

የጨዋታ ዘገባ | ዋልያዎቹ እና ጥቋቁር ከዋክብቶቹ በአምበሎቻቸው ግቦች አቻ ተለያይተዋል

አጋራ
አጋራ

በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በአፍሪካ የምድብ 5ኛ ዙር ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ ጀምረዋል ።

በምድብ 6 ከጋና ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ጋር የተመደበው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የባህር ዳር አለምአቀፍ ስታድየም መታገድን ተከትሎ በሜዳው ማድረግ የነበረበትን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ለማድረግ ተገዷል ። ጨዋታው በደቡብ አፍሪካ ሶከር ሲቲ ስታድየም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን በጨዋታውም ጥሩ መንቀሳቀስ የቻሉት ዋልያዎቹ ሲመሩ ቢቆዩም በጌታነህ ከበደ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው ጨዋታው 1 ለ 1 ሊጠናቀቅ ችሏል ።

ዋልያዎቹ በመጀመሪያ አሰላለፍ በግብ ጠባቂ ቦታ ተክለማርያም ሻንቆን በተከላካይ አስቻለው ታመነ ምኞት ደበበ ረመዳን የሱፍ እና አስራት ቱንጆ በመሀል አማኑኤል ዮሀንስ ሽመልስ በቀለ እና መሱድ መሀመድ እንዲሁም በአጥቂ አቡበከር ናስር ጌታነህ ከበደ እና ዳዋ ሆጤሳን በማሰለፍ ጀምረዋል ።

በመጀመሪያው አጋማሽ ኳስን ከኋላ መስርተው በመጫወት እና የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመውሰድ ወደ ፊት ለመሄድ ሲሞክሩ ተስተውሏል ። የጨዋታው የመጀመሪያው ሙከራ በ6ኛው ደቂቃ የተደረገ ሲሆን ጋናዎች ከግራ መስመር ይዘው የገቡትን ኳስ በሳጥን ውስጥ ሁለት ጊዜ ቢሞክሩትም ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ሊመልሳቸው ችሏል ። 22ኛ ደቂቃ ላይ የጋና ብሄራዊ ቡድን መሪ ያደረገውን ግብ አስቆጠረ ። ከሳጥኑ ቅርብ ርቀት ላይ የተገኘውን የቅጣት ምት አንድሬ አዩ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አዋሀደው ። በጋና ብሄራዊ ቡድን በኩል በተለይም በግራ መስመር ጫና በመፍጠር ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን ማድረግ የቻሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል በአማኑኤል ዮሀንስ በሽመልስ በቀለ እና በጌታነህ ከበደ የግብ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ማስቆጠር ሳይችሉ የመጀመሪያው አጋማሽ በጋና 1 ለ 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኳስ ቁጥጥር ብልጫን ወስደው መጫወት ችለዋል ። ወደ ግብ በመድረስ ረገድም የተሻለ መሆን የቻሉ ሲሆን በተለይም 57ኛ ደቂቃ ላይ ሽመልስ በቀለ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታው እና የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ኳስ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ። 72ኛ ደቂቃ ላይም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ የሚያደርገውን ግብ በአምበሉ ጌታነህ ከበደ አማካይነት ማስቆጠር ችሏል ። ጌታነህ ከበደ ከጋና ተከላካይ ኳስ ቀምቶ ለአቡበከር ናስር ያቀብለው ሲሆን አቡበከርም መልሶ ጥሩ ቦታ ይዞ ለነበረው ጌታነህ በማቀበል ግቡ ሊቆጠር ችሏል ።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ድንጋጤ ውስጥ የገቡት ጥቋቁር ከዋክብቶቹ ተጨማሪ ግብ በማስቆጠር ጨዋታውን አሸንፈው ለመውጣት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል ። የምድቡ ሌላ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በደቡብ አፍሪካ እና በዚምባቡዌ መካከል የሚደረግ ሲሆን ባፋና ባፋናዎች ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉ ወደ ቀጣይ የማለፍ ዕድላቸውን የሚያሰፉ ይሆናል ።

ዋልያዎቹ በቀጣይም የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታቸውን ዕሁድ በሀራሬ ከዚምባቡዌ ጋር በማድረግ ውድድራቸውን ያጠናቅቃሉ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...