መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ” አጀማመራችን ከባድ ቢሆንም ያን ያህል የጎላ ድክመት አልነበረብንም ” ያሬድ ሀሰን /አዲስአበባ ከተማ/
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዲስአበባ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

” አጀማመራችን ከባድ ቢሆንም ያን ያህል የጎላ ድክመት አልነበረብንም ” ያሬድ ሀሰን /አዲስአበባ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

” የዝግጅት ጊዜ ማነስ በግልፅ በሚታይ መልኩ ጎድቶናል “

” አጀማመራችን ከባድ ቢሆንም ያን ያህል የጎላ ድክመት አልነበረብንም ” ያሬድ ሀሰን /አዲስአበባ ከተማ/

በ2011 ዓ.ም መቐለ 70 እንደርታ የሊጉ ሻምፕዮን ሲሆን የቡድኑ አባል ነበር በተጨማሪም በኢትዮጵያ መድህን ፤ በወልድያ ከተማ ፤ በድሬዳዋ ከተማ ፤ በሰበታ ከተማ ተጫውቶም አሳልፏል ። በ2014 የውድድር ዘመን ደግሞ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ላደገው የመዲናዋ ክለብ አዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ላይ ይገኛል ።
ያሬድ ሀሰን ….. ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ጋር ሰለ ወቅታዊው የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ አቋም እና ስለተለያዩ ጉዳዮች ቆይታ አድርጓል ።

ሀትሪክ : የእግር ኳስ አጀማመርክ ምን ይመስል ነበር ?

ያሬድ : እግር ኳስን እንደማንኛውም ልጅ ሰፈር ውስጥ በመጫወት ነበር የጀመርኩት ። አብነት አካባቢ ባለው አለሙ ሜዳ ነበር ስጫወት የነበረው በርካታ ተጫዋቾችን ያፈራ ሜዳ ነው። ከዛም በአሰልጣኝ መሳይ ተመርጬ ወደ አዲስ ከተማ ክለብ መግባት ችያለሁ ። ከዛም በመድህን ተስፋ ቡድን ገብቼ ለዋናውም ቡድን መጫወት ችዬ ነበር በመቀጠልም ለወልድያ ከተማ ፤ ለመቀሌ 70 እንደርታ ፤ ለድሬዳዋ ከተማ አምና ለሰበታ ከተማ አሁን ደሞ በአዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ላይ እገኛለሁ ።

ሀትሪክ : በ2011 መቀሌ 70 እንደርታ የሊጉ ሻምፕዮን የቡድኑ አባል ነበርክ እና እስኪ ስለዛን ጊዜ አጫውተኝ ?

ያሬድ : በጣም ደስ የሚል አሪፍ ጊዜ ነበር በወቅቱ ጥሩ ተጨዋቾች ነበሩ ጥሩ አሰልጣኝም ነበረን ። በቡድኑ ውስጥም የነበረው ወንድማማችነት በጣም ደስ ይል ነበረ ጥሩ ጊዜ እንደነበረንም በውጤትም ጭምር ሻምፕዮን በመሆን አሳይተናል ።

ሀትሪክ : ከሰበታ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የተዘዋወርከው ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት ነበር ። ከሰበታ ከተማ የለቀክበት ምክንያት ምን ነበር ?

ያሬድ : ወደ ሰበታ ከተማ ኢንስትራክተር አብርሀም ነበር የወሰደኝ በዛም ሁለት አመት ፊርማ ነበር የፈረምኩት ። አሰልጣኙም ከአንድ አመት በኋላ ወደ ባህር ዳር ሲሄድ ቀጥሎ የመጣው አሰልጣኝ በ2014 ውል ኖሮአችውም ከማይጠቀምባቸው ወይም ከማይፈልጋቸው ተጫዋቾች አንዱ እኔ ነበርኩ ።

ሀትሪክ : የአሰልጣኙ የዕቅዱ አካል አልነበርክም ማለት ነው ?

ያሬድ : አዎ የ2014 ቡድኑን ሲገልፅ የዕቅዱ አካል አልነበርኩም ። እኔ ብቻ አልነበርኩም ሌሎችም ነበሩ ቃልኪዳን በወላይታ ድቻ ያለው እንደኔ በተመሳሳይ ነው የለቀቀው ።

ሀትሪክ : ከሰበታ ከተማ ጋር እንደማትቀጥል ካወክ በኋላ እና ወደ አዲስ አበባ ከተማ ከመዘዋወርክ በፊት ወደ ሌሎች ክለቦች የመሄድ እድሉ አልነበረክም ?

ያሬድ : ሰበታ ከተማ ከሌሎቹ ዘግይቶ ነበር አሰልጣኙን ያሳወቀው በወቅቱ ደሞ አብዛኞቹ ክለቦች ቡድናቸውን እያዘጋጁ ነበር እና በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ነበር ያመራሁት ።

ሀትሪክ : የአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱ እንዴት ነበር ?

ያሬድ : አዲስ አበባ ከተማ እንደሚታወቀው በቂ የዝግጅት ጊዜ አልነበረውም ከተጫዋቾች ምርጫ ጋር ተያይዞም ቶሎ አላለቀም ነበር ። የሲቲ ካፕ ውድድር እንኳን ስናደርግ የስምንት እና የዘጠኝ ቀን ዝግጅት ብቻ አድርገን ነበር ወደ ውድድሩ የገባነው ይህ በቂ ያልሆነው የዝግጅት ጊዜም ጎድቶናል ብዬ አስባለሁ በሊጉ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታ የታየውም እሱ ነው በሲቲ ካፑም ቢሆን ምንም ያሸነፍነው ጨዋታ አልነበረም ። ነገር ግን ቡድኑ በወጣት የተገነባ እንደመሆኑ ጊዜው ሰፋ ቢል ጥሩ ነበር ግን አሁንም ቢሆን ቡድኑ ነው ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ጥሩ እየሆነ እየመጣ ያለ ነው ።

ሀትሪክ : ስለዚህ በሲቲ ካፑም ሆነ በሊጉ ጅማሮ የታየው ደካማ እንቅስቃሴ ዋናው መንስኤ የዝግጅት ጊዜ ማጠር ነው ብለን መደምደም እንችላለን ?

ያሬድ : አዎ ምንም ጥያቄ የለውም ከዝግጅት ጊዜ ማነስ የመጣ ነው ። ማለት ረጅም ጊዜ አርፈክ ስለምትመጣ ሁለት ወር እና አንድ ወር ተኩል ተዘጋጅቶ ከመጣ ቡድን ጋር ብዙ ልዩነት ይኖራል ይሄ ደሞ የታወቀ ነው ። አንተ በግልህ በአካባቢህ ልትዘጋጅ ትችላለህ ግን ያ የምታደርገው ዝግጅት እና በአሰልጣኝ ስር ከቡድን ጋር አንድ ላይ የሚኖረው በጣም የተለያየ ነው በውድድሩ ጥሩ ለመሆንም አስፈላጊ የሚሆነው በአሰልጣኝ ስር ሆነህ የምትሰራው ነው ። የዚህ ማነስም በግልፅ በሚታይ መልኩ ጎድቶናል ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተሻሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ።

ሀትሪክ : ሊጉ ከተጀመረ በኋላ በቡድኑ ውስጥ የተፈጠረ ውዝግብ ነበር ይህ ነገር በቡድኑ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ አለ ?

ያሬድ : በጣም የሚገርምህ ቡድኑ በወጣት የተገነባ ሆኖም ብዙ የመረበሽ ስሜት አላየሁበትም ያ ከኋላ የተፈጠረውን ችግር እዛው ወደ ለኋላው የተወው ነው የሚመስለኝ ማለት ይህ ነገር ውድድር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ነው የሚያመጣው ቀላል ነገር አይደለም ግን ያን ያህል ተፅዕኖ አልፈጠረብንም ብዬ አስባለሁ ተፅዕኖ ቢፈጥርብን ኖሮ በጣም እንቸገር ነበር ። ያው የተወሰነ የምትደናገረው ነገር ሊኖር ይችላል ነገር ግን ያን ያህል አልነበረም ለዚህም ተጫዋቾቹ በጣም ሊደነቁ ይገባቸዋል ገና ወጣት ሆነው ለፕሪሚየር ሊጉም አዲስ ሆነው ይህን ነገር መቋቋሟቸው ሊመሰገኑ የሚገባ ነገር ነው እንደ ቀልድ የሚታይ ነገር ስላልሆነ ማለት ነው ።

ሀትሪክ : ከአሰልጣኙ መሰናበት ጋር በተያያዘ ምን የምትለው ነገር አለ ?

ያሬድ : እኔ ለቡድኑ አዲስ የመጣሁ ልጅ ነኝ ብዙም እዚህ ውስጥ የማውቀው ነገር የለም ። ግን እንደ ቡድን ተግባብተህ እየቀጠልክ አንድ ሰው ሲጎል የሚሰማክ ነገር ይኖራል ባይሆን የምትለው ነገር ሊኖር ይችላል ግን ሌላ ውስጡን የማውቀው ነገር ስለሌለ እንዲ እንዲህ ነው ብዬ ለመናገር የምችለው ነገር የለም ።

ሀትሪክ : በሊጉ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ሶስተኛ ሳምንት ላይ ሳይጠበቅ መከላከያን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችላችሁ ነበር ። ምን የተቀየረ ነገር ቢኖር ነው ?

ያሬድ : ከባህርዳር ጋር ስንጫወት ራሳችን በሰራናቸው ስህተቶች ነው የተሸነፍነው ያው ባህርዳር ከተማ እንደምታውቀው የተደራጀ ቡድን ነው ሊጉ ውስጥም አሪፍ ከሚባሉት ክለቦች አንዱ ነው ። ጨዋታው ከባድ ቢሆንም በስህተቶች ነው የተሸነፍነው ብዬ ነው የማምነው ። ከአርባምንጭ ከተማም እየመራን ነው የተሸነፍነው በመጀመሪያው አጋማሽ መርተን ወተን በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ገብቶብን ነው 2 ለ 1 የተሸነፍነው ። አጀማመራችን ከባድ ቢሆንም ያን ያህል የጎላ ድክመት አልነበረብንም ። ሶስተኛ ጨዋታ ግን ያን አርመን ዛሬ ሊጉን መጀመር አለብን ብለን ነው የገባነው በሁለቱ ጨዋታዎች ስለተሸነፍን በዕልህ ነበር የገባነው ። የጨዋታዎችንም ቪዲዮዎችም የባህርዳርንም የአርባምንጭንም ተመልከተን የግድ ማሸነፍ አለብን አቻ እንኳን መውጣት የለብንም ብለን ነው ወደ ጨዋታው የገባነው እና ደሞ ሜዳ ውስጥ የገባነው ልጆች ውጤቱን ይዘን ለመውጣት መስዋዕትነት ከፍለናል ሜዳ ውስጥ ብቻ ያለነው ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ ተጠባባቂ ላይ የነበረው ጉጉት የሚገርም ነበር ጎል ስናገባ ስንሞክርም ከነሱ የምንሰማው ድምፅ ነበር ። ያው ማድረግ የሚገባንን አድርገን ሶስት ነጥቡን ማሳካት ችለናል ።

ሀትሪክ : ሊጉ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይመለሳል እና አዲስ አበባ ከተማን ከዚህ በኋላ በሚኖሩ ጨዋታዎች ላይ በምን መልኩ እንጠብቀው ?

ያሬድ : ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ የመጣ ቡድን ነው ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታችንን ማሸነፋችን ከእረፍት በኋላ ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች ትልቅ ስንቅ ነው የሚሆነው ከዚህ በኋላም አሪፍ ነገር እናሳያለን ። በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍም ውስጥ ድክመቶቻችንን እያየን ነው ተጫዋቾቹም አሪፍ ላይ ናቸው በቀጣይ ጨዋታዎች ከፈጣሪ ጋር አዲስ አበባ ከተማ ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ የሚመጣ ቡድን ነው ብዬ አስባለሁ ።

ሀትሪክ : ቀጣይ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታቹ ከአምናው ሻምፕዮን እና አሁንም የሊጉ መሪ ከሆነው ፋሲል ከተማ ጋር ነው እና ለዚህ ጨዋታ ምን ያህል ትዘጋጃላቹ ?

ያሬድ : እስካሁን ለዚህ ቡድን እንደዚህ ነው የምንሰራው ለዛኛው እንደዚህ ነው የምንሰራው ብለን አይደለም ያለነው ሁሉንም ቡድን እንደ አንድ ነው የምናየው ። ግን ያው እንደምታውቀው ፋሲል ጠንካራ ቡድን ነው ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎችንም በማሸነፍ ሊጉን እየመራ የሚገኝ ቡድን እንደመሆኑ በአዕምሮ ደረጃ ጠንካራ ጨዋታ ከፊታችን አለ ብለን እንጂ የተለየ የምናደርገው ዝግጅት አይኖርም ።

ሀትሪክ : በእግር ኳስ ህይወትክ በጣም የተደሰትክበት እና ያዘንክበት አጋጣሚ ?

ያሬድ : በእግር ኳስ ህይወቴ ብዙ ደስታዎች አሉ ግን በጣም የተደሰትኩበት በ2011 ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር የሊጉ ሻምፕዮን ስንሆን ነው ያዘንኩበት ደግሞ በወልድያ ከተማ እያለሁ ወልድያ ከተማ ከሊጉ የወረደበት ጊዜ በጣም የሚቆጨኝ እና ያዘንኩበት ነው ።

ሀትሪክ : አርአያዬ ነው የምትለው ተጫዋች ማነው ?

ያሬድ : ብዙ አሉ ግን ያው መጀመሪያ የምታየው ሰፈርክ በቅርብክ ያለውን ነው ። አንደኛው ጅላሉ ሻፊ ነው ብዙ ክለቦች ተጫውቷል የሰፈሬ ልጅም ስለሆነ እያየሁትም ስላደኩኝ በጣም ነበር የማደንቀው እና እሱ ነው አርአያዬ ።

ሀትሪክ : ያሬድ እግር ኳስ ተጫዋች ባይሆን ምን ይሆን ነበር ?

ያሬድ : ( ሳቅ ) እግር ኳስ ተጫዋች ባልሆን እግር ኳስ ተጫዋች ነበር የምሆነው ከዛ አልወጣም ። እግር ኳስን ብቻ ነው የማስበው ።

ሀትሪክ : በሊጉ ማልያውን ለብሼ ልጫወትበት እፈልጋለሁ የምትለው ክለብ ይኖር ይሆን ?

ያሬድ : ( ሳቅ ) አለ ግን እኔ ጋር ይቆይ

ሀትሪክ : በእግር ኳስ ማሳካት የምትፈልገው የኔ ግብ የምትለው ነገር ምንድነው ?

ያሬድ : መጀመሪያ የጎደለኝን ነገር አስተካክዬ ጥሩ ተጫዋች መሆን ነው የማስበው እና የብሄራዊ ቡድን ማልያ መልበስ ያው ይሄ የብዙ ተጫዋቾች ምኞት ነው እኔም የተሻለ ነገር ሰርቼ የሀገር ጥሪ ተቀብዬ የብሄራዊ ቡድኑን ማልያ ለብሼ መጫወት ነው ህልሜም አላማዬም ።

ሀትሪክ : ከሀገር ውስጥ የምታደንቀው ተጫዋች ማነው ?

ያሬድ : ከሀገር ውስጥ በጣም የማደንቀውም አብሬው በመጫወቴም የምደሰትበት ተጫዋች ዳዊት እስጢፋኖስ ነው ። ለሱ ትልቅ ክብር አለኝ ።

ሀትሪክ : ለያሬድ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ወይስ ክርስትያኖ ሮናልዶ ?

ያሬድ : ( ሳቅ ) ምንም ጥርጥር የሌለው ሜሲ ነው

ሀትሪክ : በመጨረሻም ምስጋና የምታቀርብላቸው አካላት ካሉ ?

ያሬድ : መጀመሪያ ማመስገን የምፈልገው ልዑል እግዚአብሔርን ነው እዚህ ያደረሰኝን ማለት ለኔ ትልቅ ስጦታ ነው በእግር ኳስ ህይወት ውስጥ መኖር ይህን የሰጠኝን እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ ሁለተኛ ሁሌም በሀሳብም በሁሉም ነገር አብረውኝ ላሉት የሰፈሬ የአብነት ልጆች ልዩ ምስጋና አለኝ በመጨረሻም ከሰፈሬ አንስቶ ዛሬ ላለሁበት ደረጃ እንድደርስ ትልቅ አስተዋፅኦ ላደረገልኝ አሰልጣኝ መሳይ ትልቅ አክብሮት እና ምስጋና አለኝ ።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...