መነሻ ገጽ አፍሪካ ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የትልቁን መድረክ የፍፃሜ ጨዋታ እንደምትመራ ታዉቋል!!
አፍሪካአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግዜናዎች

ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የትልቁን መድረክ የፍፃሜ ጨዋታ እንደምትመራ ታዉቋል!!

አጋራ
አጋራ

በግብፅ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ በሚገኘዉ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዩንስ ሊግ የመጀመሪያውን ፍፃሜ ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ እንደምትመራዉ ተረጋግጧል።

በየዞናቸው በነበሩ ዉድድሮች ላይ ቀዳሚቁን ስፍራ ይዘዉ ያጠናቀቁት ስምንት ክለቦች በሚሳተፉበት በዚህ ዉድድር ላይ ዳኛዋ ከዚህ ቀደም ሁለት(1በዋና ዳኝነት 1በአራተኛ ዳኝነት) ያህል ጨዋታዎችን መምራቷ ይታወሳል።

እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፉክክር በነበረበት በዚህ ምርጫ የብቃት ጣሪያዋ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ በነገዉ ዕለት በጋናዉ ሀሳካስ ሌዲስ እና በደቡብ አፍሪካዉ ማሚሎዲ ሰንዳዉስ መካከል የሚደረገዉን ነፍፃሜ ጨዋታ ከግብፅ ፣ ሞሪታኒያ እና ናይጀሪያዉያን ረዳቶቿ ጋር በመሆን እንደምትመራ ተረጋግጧል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያን በትልልቅ መድረክ እየወከለች ያለችዉ ሊዲያ የፍፃሜዉን ጨዋታ እንድትመራ መመረጧ እጅግ ከፍተኛ ደስታን እንደፈጠረላት እንዲሁም ከሁሉ አስቀድማ ፈጣሪዋን እንደምታመሰግን ገልፃለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...