በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጎልተው ከወጡ ወጣት ተጫዋቾች አንዱ ነው ፀጋአብ ዮሐንስ በወጣትነት እድሜ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት እየመራም ይገኛል ።ስለ እግር ኳስ ህይወቱ ስለ ብሔራዊ ቡድን እና ስለ ፕሪምየር ሊግ ከሀትሪክ ጋር ቆይታ አድርጓል።
እግር ኳስን የት እና እንዴት ጀመርክ?
ፀጋአብ:- እግር ኳስን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጨርቅ ኳስ በመጫወት ነው የጀመርኩት ሰፈራችን ቄራ ሜዳ አካባቢ ስለሆነ አብዛኛውን ጊዜዬን እዛ በመጫወት ነው የማሳልፈው።
በክለብ ደረጃ እንዴት መጫወት ጀመርክ?
- ማሰታውቂያ -
ፀጋአብ:-ቄራ ሜዳ በየአመቱ የሚዘጋጅ የፕሮጀክት ውድድር አለ :በውድድሩ ላይ ራስ በተስፋ ፕሮጀክትን ወክዬ መጫወት ጀመርኩ በውድድሩ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ስላሳየው የሀዋሳ ከነማ ቢ ቡድን አሰልጣኝ ብርሀኑ ወርቁ ለቢ ቡድን መረጠኝ ።እንግዲህ ይሄን ይመስላል የክለብ ጅማሬዬ
በቢ ቡድን ያለህን ቆይታ አጫውተኝ
ፀጋአብ:-ቢ ቡድን ላይ በጣም ጥሩ ጊዜ ነበረኝ ሁለቱንም ዓመት ሻምፒዮን ነበርን : በተጨማሪ ብሩንዲ ላይ በተዘጋጀው ከ17 ዓመት በታች ሴካፋ ውድድርም ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ ችያለሁ
ከዚህ በኋላ ነው የሀዋሳ ዋናውን ቡድን የተቀላቀልከው ?
ፀጋአብ:-አይደለም ከቢ ቡድን ወደ ተስፋ ቡድን ገባው ከዛ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ በተዘጋጀው ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ለብሔራዊ ቡድን ተጠራው : ቡድኑንም በአምበልነት መራው ።ከብሔራዊ ቡድን እንደተመለስኩ ለሀዋሳ ዋናው ቡድን ተጠራው
ለብሔራዊ ቡድን ስትጠራ ምን ተሰማህ?
ፀጋአብ:-የተሰማኝን ስሜት በቃላት ልገልፅልህ አልችልም ። በእግር ኳስ ህይወቴ ትልቁ ምኞቴ የሀገሬን ማልያ መልበስ ነበር ያ ህልሜ ቶሎ በመሳካቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለው።
የመጀመሪያ ዓመት የሀዋሳ ከነማ ቆይታህ እንዴት ነበር?
ፀጋአብ:-የመጀመሪያ ዓመት ቆይታዬ እንደፈራሁት ከባድ አልነበረም : ወደ ቡድኑ ስቀላቀል የቡድናችን አምበል ዳንኤል ደርቤ እና አስጨናቂ ሉቃስ ነገሮች እንዲቀሉኝ በብዙ መንገድ ሲያግዙኝ ነበር ከእነሱ በተጨማሪም የቡድናችን አሰልጣኝ እና ሲኒየር ተጫዋቾችም አግዘውኛል።
በመጀመሪያው ዓመትህ በሀገራችን ትልቁ ሊግ ላይ ቋሚ ሆኖ የመጫወት አድል አግኝተኸል : ምን ስሜት ተሰማህ?
ፀጋአብ:-ስሜቱ የተደበላለቀ ነበር ምክንያቱም ከልጅነቴ ጀምሮ የሀዋሳ ከነማን ማልያ ለብሼ በፕሪምየር ሊጉ ለመጫወት ሳልም ነበር ይህም በመሳካቱ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።
የወደፊት ህልምህ ምንድነው?
ፀጋአብ:-የወደፊት ህልሜ ሀዋሳ ከነማን ሻምፒዮን ማድረግ እና በፕሮፌሽናል ደረጃ ከሀገር ወጥቶ መጫወት የሁልጊዜ ህልሜ ነው።
ዘንድሮ DSTV ወደ ሀገራችን መጥተዋል ምን ተሰማህ
ፀጋአብ:-እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ ራሳችንን ለማሳየት ጥሩ እድል ይዞልን መቷል ብዬ አስባለው።
DSTV በመጣበት ዓመትም ብዙ የመጫወት አድል አግኝተኸል እና ራሴን በሚገባ አሳይቻለው ብለህ ታስባለህ?
ፀጋአብ:-አዎ : ለክለቤ የምችለውን ሁሉ አድርጌያለሁ ራሴንም በሚገባ ለማሳየት ተጠቅሜበታለው
በዘንድሮው የውድድር ዓመት ሁሉንም የኮከብነት ዋንጫዎችን ስላነሳው አቡበከር ናስር ምን ትላለህ?
ፀጋአብ:-በእውነቱ አቡኪ የልፋቱን ውጤት ነው ያገኘው ብዬ አስባለሁ በእሱ እድሜ ሀገራችን ላይ የእሱን ያህል የተሳካለት ተጫዋች አለ ብዬ አላስብም ።ለእሱ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል
ለእናንተ ለወጣቶቹ አርአያ ነው ብለህ ታስባለህ?
ፀጋአብ:-በሚገባ ነዋ: እርግጠኛ ነኝ እሱ ያዩ አሰልጣኞች ለወጣቶች እድል መስጠት ይጀምራሉ ብዬ አስባለሁ
ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የማን አድናቂ ነህ?
ፀጋአብ:-የአስቻለው ታመነ እና የሊዮኔል ሜሲ
ከክለብስ?
ፀጋአብ:-የሀዋሳ ከነማ እና የባርሴሎና
የክለባቹ አዝናኙ ተጫዋች ማነው?
ፀጋአብ:-ኤፍሬም ዘካሪያስ ነው በቃ እሱ ባለበት ሁሌም
ሳቅ አለ
በመጨረሻ ማመስገን የምትፈልጋቸው ካሉ
ፀጋአብ:-በመጀመሪያ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግናለው በመቀጠል ቤተሰቦቼን ማመስገን ፈልጋለው ። አሰልጣኝ ሲሳይ ደቦጭ : ብርሀኑ ወርቁ:ተመስገን ዳና : ሙልጌታ ምህረት እና በፕሪምየር ሊጉ አምኖብኝ አድሉን የሰጠኝን አዲሴ ካሳን አመሰግናለው ።በመጨረሻ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ በብዙ ነገር ሲረዳኝ የነበረውን ፊዚዮትራፒ ብሩክ ደበበን አመሰግናለው ።እናንተንም ከልብ አመሰግናለው።