ላለፉት ሶስት ያህል አመታት በዕድሳት ላይ የሚገኘዉ አንጋፋው የአዲስአበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራዉ ተጠናቆ ከወራት በኋላ ማለትም ከህዳር ጀምሮ የፕሪምየር ሊግ እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እንደሚደረጉበት ተገልጿል።
ረጅም ጊዜያትን በዕድሳት ላይ ይገኝ የነበረዉ ስታዲሙ በወራት ውስጥ የዕድሳት ጊዜዉ ተጠናቆ የሊጉ ጨዋታዎች ፣ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እና አትሌቶች ጭምር በነፃነት ልምምድ እንደሚያደርጉበት የኢፌድሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስተሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ19ነኛዉ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለነበሩ አትሌቶች ሽልማት ባበረከተበት ምሸት ተናግረዋል።
እንደሚታወሰዉ ከቀናት በፊት ወደ ግብፅ አምርቶ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በስታዲየሙ ላይ ለምምድ ማድረጉ ይታወቃል።