ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እየተመሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ እያደረጉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ የአሰልጣኝ ክፍላቸዉን ወደማጠናከር ገብተዋል።
ሲዳማ ቡናዎች የቀድሞዉን የሀዋሳ ከተማ ስፖርት መምሪያ የስፖርት ማህበራት እዉቅናና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ እና የሲዳማ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ሀላፊ እንዲሁም የፅህፈት ቤት ሀላፊ በመሆን ያገለገለዉን አቶ አለሙ ኤሮሞን የክለባቸዉ ቡድን መሪ አድርገዉ ቀጥረዋል።