በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመራ ለአዲሱ የውድድር አመት ዝግጅቱን በመቀመጫ ከተማዉ እያደረገ የሚገኘዉ ሀዋሳ ከተማ የቀድሞዉን የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ቻርልስ ሉክዋጎ ማስፈረሙ ታውቋል።
ከዚህ ቀደም በሀገሩ ዮጋንዳ ሊግ በርከት ላሉ ክለቦች መጫወት የቻለዉ እንዲሁም በፈረሰኞቹ ቤት ደግሞ በጥሩ ብቃት ያለፉትን አመታት ማገልገል የቻለዉ እና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከክለቡ ጋር የተለያየዉ ዩጋንዳዊዉ ግብ ጠባቂ ቻርልስ ሉክዋጎ በመጨረሻም ማረፊያው ሀዋሳ ከተማ ሆኗል።