በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እየተመሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ቅድመ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ እየሰሩ ቆይተዉ ሲዳማ ጎፈሬ ካፕ ላይ ተሳትፈዉ የሁለተኛ ደረጃ ዪዘዉ በማጠናቀቅ ለ2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዉድድር ዘመን ወደ አዳማ ከተማ ያመሩት ሲዳማ ቡናዎች የጋና ዜግነት ያለዉ የመስመር አጥቂ አስፈርመዋል።
ሲዳማ ቡናዎች በቅድመ ዉድድር ጊዜያቸዉ አብሯቸዉ የሙከራ ጊዜ ሲያሳልፍ የነበረዉን ሚካኤል ኬፕሮቪን በአንድ አመት ኮንትራት ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
አዲሱ የሲዳማ ቡና ፈራሚ ከዚህ በፊት ለጋና ክለቦች ሶንዲሶ እና ኢንተር አላይንስ በመቀጠልም ለሴኔጋሉ ኤ ኤስ ሲ ጂርፍ ፣ ለሱዳኑ ኤልሜሪክ ፣ ለአይቮሪኮስቱ አፍሪካን ስፖርትስ መጫወት የቻለ ሲሆን እንዲሁም ያለፉትን አራት ዓመታት ለህንዱ ቢ ኤስ ኤስ እና ለኔሮካ ተጫዉቷል።
- ማሰታውቂያ -