መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ እግርኳስ ክለብና ዳሽን ቢራ ለቀጣዩ አምስት አመት አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማ እግርኳስ ክለብና ዳሽን ቢራ ለቀጣዩ አምስት አመት አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ

አጋራ
አጋራ

ከፋሲል ከነማ ስኬት ጀርባ ዳሽን ቢራ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው”
አቶ አቢዮት ዓለሙ
የፋሲል ከነማ ዋና ስራ አስኪያጅ

“በፋሲል ያገኘነው ጥቅም በቀላሉ የሚለካ አይደለም እኛም በፋሲል ሻምፒዮን ነን”

አቶ አብርሃም ዘሪሁን
የዳሽን ቢራ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ

በሸራተን አዲስ በተካሄደው በዚህ የፊርማ ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው በቀጣይ አምስት አመታት ዳሽን ቢራ ለፋሲል 136 ሚሊየን ብር በስፖንሰርሺፕ ስምምነት ክፍያውን እንደሚፈጽም አስታውቋል።
አንደኛ ከወጡ 2 ሚሊዮን ሁለተኛ ከሆኑ 1ሚሊዮን ብር ጉርሻ እንደሚሰጥና ክለቡ የገቢ ማሰባሰቢያ ብሎ በሚያዘጋጀው ኮንሰርት ሩጫና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይም ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል። ዳሽን ቢራ ባለፉት 20 አመታት በህብረተሰብ አቀፍ አስተዋጽኦ ወደ 800 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉም ተጠቅሷል።

“ከፋሲል ከነማ ጋር ባለፉት አምስት አመታት በነበረ ውል መሠረት ክለቡ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረ ሲሆን
በመጀመርያ ሁለት አመት ዋንጫ ማንሳት እየቻለ እግርኳሳዊ ባልሆነ ምክንያት አጥቶ ዘንድሮ ግን አሳክቷል የአሁኑ ውል ደግሞ ሻምፒዮንነቱን ከማስቀጠል በተጨማሪ በአፍሪካ ደረጃ ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግም የሚያስችል ነው” ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ አብርሃም ዘሪሁን ገልጸዋል።

እንደ አቶ አብርሃም “ባለፉት አምስት አመታት የፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪና ሻምፒዮና ሲሆን ለብሄራዊ ቡድን በርካታ ተጨዋቾቾን በማስመረጥ ትልቅ አሻራ ሲጥል ዳሽን ቢራ ከጎኑ በመሰለፉም ጭምር በመሆኑ ደስተኞች ነን ሲሉ ገልጸዋል። “የፋሲል ጥቅም በገንዘብ ብቻ የሚለካ አይደለም የመጀመርያ ፋብሪካ የከፈትነው ጎንደር ሲሆን ፋሲልን መደገፍ ማህበረሰቡን መደገፍና ሻምፒዮን ሲሆን እኛም ሻምፒዮን እንዳደረገን መታሰብ አለበት” ሲሉ አቶ አብርሃም አስረድተዋል።

የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አቢዮት ብርሃኑ በበኩላቸው” በክለብ ደረጃ ራስን በፋይናንስ ማጠናከር የግድ ነው የከነማ ክለቦች እንደ ሌሎች የግል ክለቦችና የገንዘብ ችግር እንደማይነሳባቸው ክለቦች ናቸው ማለት ይከብዳል። ለዚህም በቀጣዮቹ አምስት አመታት ከዳሽን ቢራ ጋር የፈረምነው ውል ትልቅ ትርጉም አለው የምንለው… ፋሲል በዳሽን ቢራ ዳሽን ቢራም በፋሲል የምንተጋገዝበትና የምንጠቃቀምበት ውል በመሆኑ ደስተኞች ነን ከፋሲል ከነማ ስኬት ጀርባ ዳሽን ቢራ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው… በክለቡና በደጋፊዎቻችን ስም ዳሽን ቢራን አመሰግናለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...