By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: ለቅዳሜ የተጠራው የአ/አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠ/ጉባኤ እያወዛገበ ነው ….
Share
Notification Show More
Latest News
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ለቅዳሜ የተጠራው የአ/አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠ/ጉባኤ እያወዛገበ ነው ….

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

👉… ጉባኤውን ፕሬዝዳንቱ የማያውቁት በጽ/ቤት ሃላፊዋ የተጠራ መሆኑ ቅሬታ ፈጥሯል…

👉…የወጣቶችና ስፖርት ጣልቃ ገብነት ተንጸባርቆበታል እየተባለ ነው…..

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ያለ አግባብ ጣልቃ መግባቱ ቁጣ ቀስቅሷል።

ቢሮው በፌዴሬሽኖች የውስጥ አሰራር ጣልቃ በመግባት የሚወስናቸው የማንአለብኝነት ውሳኔዎች ቅሬታ እየፈጠረ ሲሆን ከሰሞኑ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩጽ እውቅና ውጪ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬና አራት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ለህዳር 22/2016 የጠሩትን ጠቅላላ ጉባኤ መቀበሉ አስገራሚ ተብሏል።

- ማሰታውቂያ -

በትውልደ ኢትዮጵያዊ ስም የካናዳ ዜግነት ያላቸውን ፕሬዝዳንቱን አቶ ቢኒያምን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ የከተማው የስፖርት ም/ቤት ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ፕሬዝዳንት እንዳይሆኑ ተወስኗል በሚል የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት ከንቲባ አዳነች አበቤ ፊርማ ያላረፈበትን ህግ በመጥቀስ የቢሮው ም/ል ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እየሰጡት ያለው ተገቢ ያልሆነ አመራር ቅሬታ ፈጥሯል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ቢሮው ጣልቃ ገብቷል ይሄን ማስተካከል አለብን በማለት መጀመሪያ ጥቅምት ተጠርቶ የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲራዘም ቢያደርጉም ምንም አይነት የማስተካከያ ርምጃ መውሰድ ሳይችሉ በጽ/ቤት ሃላፊዋ በኩል ጉባኤው ሲጠራ ዝምታን መምረጣቸው መፍቀዳቸውን ያሳያል በሚል እየተተቹ ነው።

የጽ/ቤት ሃላፊዋ ወ/ሮ እታፈራሁ በፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትና አመራሮች ፍቃድ ለ19ኛው የሀንጋሪ ቡዳፔሽት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲመለከቱ ወጪያቸው ተችሎ እንዲጓዙ የተደረጉ ከፌዴሬሽኑ ሊነሱ ሲሉ በአቶ ቢኒያም ብርታት የቀሩ ቢሆንም አሁን ግን ከፕሬዝዳንቱ ጀርባ የቢሮውን ሃላፊዎች አላማ የሚያስፈጽሙ ሆነዋል ተብሏል። የጽ/ቤት ሃላፊዋ ያለስልጣናቸው ያለፕሬዝዳንቱ ፍቃድ ካፈነገጡ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራታቸው የሚያስጠይቃቸው እንደሆነ ከቢሮውና ፌዴሬሽኑ የቅርብ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

እንደ ቢሮው ሃላፊነት የተንጋደደውን አካሄድ ማስተካከል የከተማ አስተዳደሩን ስም ከመጠበቅና ህግና ደንቦችን ከማስከበር ይልቅ በም/ል የቢሮው ሃላፊ ጥላ ስር የሆኑት ዋና ሃላፊው ጠቅላላ ጉባኤው በህገወጥ መንገድ ሲጠራ ዝምታን መምረጣቸው ጥርስ የሌላቸው አንበሳ ሆኑ እንዴ የሚያስብል ጥያቄ አስነስቶባቸዋል።

በትውልደ ኢትዮጵያዊ ስም በቢሮው ሃላፊዎች የተገፉት አቶ ቢኒያም  የስመጥሩው የአትሌቲክስ ሰው ማርሽ ቀያሪው ምሩጽ ይፍጠር ልጅ ሲሆኑ ፌዴሬሽናቸው በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር ካሉ 36 ፌዴሬሽኖች መሃል ባለፉት 3 ተከታታይ አመታት አንደኛ ሆኖ መመረጡ ታውቋል። አቶ ቢኒያም የቢሮውን ሃላፊዎች ጣልቃ ገቢ እጅ ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣና ህግ እንዲከበር ደንብ እንዲተገበር ማድረጋቸው በቢሮው ሃላፊዎች ጥርስ እንዲነከስባቸው ሳያደርግ እንዳልቀረ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

ባለፉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን ሲመሩ የነበሩ አራት አመራሮች ለአቶ ቢኒያም መብት ከመሟገት ይልቅ ራሳቸውን ከቢሮው ሃሳብ ጋር በማስኬድ ከጽ/ቤት ሃላፊዋ ጋር በመሰብሰብ ምልአተ ጉባኤ ባልተሟላበት በድብቅ ተነጋግረው ለፊታችን ቅዳሜ በቫይብስ ሆቴል የጠሩት ጉባኤ ሁሉንም ያላማከለና ለአሰልጣኞችና ለኤሊት አትሌቶች ማህበር ጥሪ ሳያደረጉ ጥሩው ለክለቦች ብቻ መድረሱ የህጋዊነትና የተቀባይነት ጥያቄ ሊነሳበት እንደሚችል ተገምቷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ የሆኑት አምባሳደር መስፍን ቸርነትም ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን የሚከለክለው መመሪያ ካለም በብሄራዊ ፌዴሬሽኖች እንጂ በክልልና ከተማ አስተዳደር ፌዴሬሽኖች የሃላፊነት ቦታ አይደለም በሚል ማብራሪያ ቢሰጡም የወጣቶችና ስፖርት የቢሮ ሃላፊዎች ሊተገብሩት አለመቻላቸው ሃላፊነትን ለግል ሃሳብ ለማዋል ከማሰብ ውጪ የተለየ ትርጉምን አይሰጠውምም እየተባለ ነው።

“የአዲስ አበባ የስፖርት ም/ቤት መመሪያ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዲያስፖራ አዋጅ በላይ ሊሆን አይችልም” የሚሉት የህግ ሰዎች ደግሞ “መመሪያው ቢጸድቅ እንኳን ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በቀጣዩ አመት እንጂ ወዲያውኑ የሚተገበርበት አግባብም የለውም” ሲሉ ይከራከራሉ።

ቅዳሜ የተጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የመካሄዱ ነገር ጥያቄ ቢነሳበትም 3 ፕሬዝዳንታዊና 14 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በዕጩነት መቅረባቸው ታውቋል።

You Might Also Like

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article “ሁለቱ ጨዋታዎች በሜዳችን ቢሆኑ ኖሮ በትንሹ አራት ነጥብ ማግኘት የምንችልበት ነበር ።” “በግል በተፈጠረ ስህተት እንጂ እንደ ቡድን ተበልጠን አይደለን የተሸነፍነው ።” “ወጣት ተጫዋቾችን መልምለን “ሻዶው” ቡድን የመስራት ዕቅድ አለኝ ።” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ
Next Article የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀትሪክ ትግርኛዜናታት ስፖርት

ሀትሪክ ትግርኛ | መበል 12 ሰሙን ዓበይቲ ፍፃመታት ኘሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ

ዳዊት ብርሀነ By ዳዊት ብርሀነ 6 years ago
የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ቡሩንድ አቻውን የሚገጥምበት አሰላለፍ ይፋ አድርጓል
የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ተካሂዷል
የጨዋታ ሪፖርት | በኢትዮጵያ ዋንጫ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጲያ ቡና ያገናኝው ጨዋታ በተሰጡ መለያ ምቶች እንግዳዎቹ ኢትዮጲያ ቡናዎች በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡
ዜና | ወላይታ ዲቻ ለነገው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ሰርቷል።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?