በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከስድስተኛው ሳምንት ጀምሮ ያሉ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ እንደሚደረጉ ይታወቃል ።
በውድድሩ አመቱ የመጀመሪያ ሳምንታት ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል አብዛኛዎቹ የዲኤስቲቪ የቀጥታ ስርጭት አለማግኘታቸው ብዙ ቅሬታዎችን መፍጠሩም አይዘነጋም ።
የሊግ አክስዮን ማህበሩ አስቀድሞ ከስድስተኛ ሳምንት ጀምሮ ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኙ ገልፆ የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መረጃም ከነገ ጀምሮ የሚደረጉት ጨዋታዎች በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በቀጥታ እንደሚተላለፉ አሳውቋል ።
- ማሰታውቂያ -
የሊግ አክስዮን ማህበሩ ከሱፐር ስፖርት ጋር ያለው ስምምነት በውድድር ዓመቱ 180 ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ መሆኑንን የገለፀ ሲሆን ከነዚህም ስምንት ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ማግኘተታቸውን ተከትሎ በቀጣይ ከሚደረጉ 200 ጨዋታዎች 172 በቀጥታ ይተላለፋሉ ብሏል ።
በተጨማሪም ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን(Artificial Intellignece) ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከስምምነቱ ውጪ ያሉ ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ አክሰዮን ማህበሩ ከሱፐርስፖርት ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል ።
በሊጉ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ከቀን 9:00 ጀምሮ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ ሀምበሪቾ ዱራሜ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ ።