ቅድመ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ እየሰሩ ቆይተዉ ለ2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዉድድር ዘመን በአዳማ ከተማ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
በዚህም መሰረት ሲዳማ ቡናዎች የቀድሞ ተጫዋቻቸዉን ሀብታሙ ገዛሀኝን እና ገዛኸኝ ባልጉዳን ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
- ማሰታውቂያ -
ሀብታሙ ገዛኸኝ ያለፈዉን የዉድድር ዓመት ከፋሲል ከተማ ጋር ማሳለፍ የቻለ ሲሆን እንዲሁም ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅቱን ከአፄዎቹ ጋር እየሰራ የቆየ ቢሆንም የአንድ አመት ቀሪ ኮንትራት እያለዉ ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት ፊርማዉን ለቀድሞ ክለቡ ለሲዳማ ቡና አኑሯል።
እንዲሁም ወደ ሲዳማ ቡና ለመግባት በሙከራ ላይ የነበረዉ የቀድሞዉ የመቻል ስፖርት ክለብ ተጫዋች የነበረዉ ገዛኸኝ ባልጉዳ ክለቡን የተቀላቀለ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል።