By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ኢትዮጵያ መድን በአቡበከር ሳኒ ሁለት ግቦች ታግዞ ሀምበሪቾ ዱራሜን ሲረታ ፤ ኢትዮጵያ ቡናም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አቻ ተለያይቷል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችኢትዮጵያ ንግድ ባንክሀምበሪቾ ድራሜየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህን

ኢትዮጵያ መድን በአቡበከር ሳኒ ሁለት ግቦች ታግዞ ሀምበሪቾ ዱራሜን ሲረታ ፤ ኢትዮጵያ ቡናም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አቻ ተለያይቷል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በሀያ ሶስተኛዉ ሳምንት ሁለተኛ ዕለት ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾ ዱራሜን ሁለት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጥቂት የሚባል የግብ ሙከራ በተስተዋለበት የሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ አጋማሽ ኢትዮጵያ መድኖች በአጠቃላይ የጨዋታዉን ብልጫ ሲወስዱ ፤ በተቃራኒው በእንቅስቃሴ ረገድ ብልጫ ተወስዶባቸዉ የነበሩት ሀምበሪቾ ዱራሜዎች ደግሞ በአጋማሹ ተጠቃሽ ሙከራም ለማድግ ሲቸገሩ ተስተውሏል። በዚህ ሁኔታ በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ጀሮም ፍሊፕ በሀምበሪቾ ዱራሜ በኩል ቀዳሚ ሙከራ አድርጎ የነበረ ቢሆንም የግብ ዘቡ ፓሉማ ፓጂ ግን በግሩም ቅልጥፍና ኳሷን መልሷል።

ተደጋጋሚ ዕድሎች ማግኘት የቀጠለዉ ኢትዮጵያ መድን በቅርቡ ክለቡን በተቀላቀለዉ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አብዱሳ ጀማል አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ቢችልም ነገር ግን አሁንም የግብ ዘቡ ኳሷን በግሩም ብቃት መልሷል። በአብዛኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ወደ ራሳቸዉ የግብ ክፍል አፈግፍገዉ በተደራጀ መከላከል በመጫዎት የተጋጣሚን ቡድን ማጥቃት በመመከት እና አልፎ አልፎ ደግሞ በመልሶ ማጥቃት አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ የነበሩት ሀምበሪቾዎች ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ ሳያደርጉ አጋማሹ ተጠናቋል።

- ማሰታውቂያ -

በሁለተኛዉ አጋማሽ ኢትዮጵያ መድን ጥሩ በመንቀሳቀስ እና ብልጫ በመዉሰድ የተሻለ የነበረ ሲሆን ፤ በሙከራ ረገድ ግን ሀምበሪቾዎች በአላዛር አማካኝነት ድንቅ ሙከራን ማድረግ ችለዉ ነበር ። በ68ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን አጥቂዉ ወገኔ ገዛኸኝ ያሻገረዉን ኳስ አቡበከር ሳኒ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ኢትዮጵያ መድንን መሪ ማድረግ ቻለ ።

ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቻሉት መድኖች በ75ተኛዉ ደቂቃ ላይ አቡበከር ሳኒ  ከአለን ካይዋ የተሻገረለትን ኳስ የግብ ጠባቂዉ ስህተት ታክሎበት ወደ ግብነት በመቀየር የክለቡን ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታዉ በኢትዮጵያ መድን ሁለት ለዜሮ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ለዜሮ ከመመራት ተነስቶ ከሊጉ መሪ ንግድ ባንክ ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል ።

በተመጣጣኝ የጨዋታ እንቅስቃሴ በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ገና በ5ተኛዉ ደቂቃ አማካዩ ባሲሩ ዑመር በቀኝ መስመር በኩል ለሚገኘዉ ሱሉይማን ሀሚድ ያቀበለዉን ኳስ ተጫዋቹ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷን የግቡ አግዳሚ ሲመልስ ያኔ አጥቂዉ ሲሞን ፒተር አስቆጥሮ ክለቡን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪ ማድረግ ችሏል።

በመጠኑም ቢሆን የጨዋታ ብልጫ ተወስዶባቸዉ የነበሩት ነገር ግን በሙከራ ረገድ የተሻሉ የነበሩት ቡናማዎቹ በቀኝ መስመር በኩል በ9ነኛዉ ደቂቃ አብዱልከሪም ወርቁ ከኋላ ያገኘዉን ኳስ ገፍቶ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም የግቡ ቋሚ ኳሷን መልሷታል። በድጋሚም በ14ተኛዉ ደቂቃ አማካዩ አብዱልከሪም በአራት የንግድ ባንክ ተጫዋች መሐል ወደ ግብ የሞከረዉን ኳስ ግብ ጠባቂዉ ፍሬዉ ጌታሁን መልሷል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም ከቀኝ መስመር በኩል አማኑኤል ዮሐንስ ከሌላኛዉ አማኑኤል አገኘዉ የተሻገረለትን ኳስ በጭንቅላቱ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ግብ ጠባቂዉ ፍሬዉ ጌታሁን እንደምንም ኳሷን አዉጥቷል። በ43ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን ባንኮች ሁለተኛ ግብ አግኝተዋል። በዚህም ከግራ መስመር በኩል ፉዓድ ፈረጃ ወደ ሳጥን ያሻገረዉን ኳስ ሳይመን ፒተር በጭንቅላቱ ወደ ግብነት ቀይሮ የክለቡን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ቢችልም ፤ ነገር ግን ተጫዋቹ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ወጥቷል።

ከዕረፍት መልስ ሁለቱም ክለቦች የተጫዋች ለዉጥ በማድረግ ጨዋታዉን ለመቆጣጠር ሲጥሩ ነገር ግን በአጋማሹ በሙከራ ረገድ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴን ሲያስመለክተን ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ያስቆጠሩትን ግብ አስጠብቀዉ በይበልጥ ደግሞ ጨዋታዉን ለመቆጣጠር ሲጥሩ ፤ በቡናማዎቹ በኩል ደግሞ ግቦችን ለማግኘት ቶሎ ቶሎ ወደ ሶስተኛዉ የሜዳ ክፍል በመድረስ ዕድሎችን ለመፍጠር ሰመጥሩ ተስተውሏል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ እጅጉኑ ጫና ወስደዉ የተጫወቱት ቡናማዎቹ በ84ተኛዉ ደቂቃ ላይ ወደ ጨዋታዉ የሚመልሳቸውን ግብ አግኝተዋል ፤ በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ ከአስራት ቱንጆ የተቀበለዉን ኳስ ከሳጥን ዉጭ ወደ መትቶ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በዚህ ሂደት ተፋፍሞ በቀጠለዉ ጨዋታ በጭማሪው 90+2 ደቂቃ ላይም ከኋላ መስመር የተሻገረዉን ኳስ አንተነህ ተፈራ ለመስፍን ታፈሰ አቀብሎት ተጫዋቹ ደግሞ በሚደንቅ ሁኔታ ኳሷን እንደምንም ብሎ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡ ወሳኝ አንድ ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎ ጨዋታው ሁለት አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የሻሸመኔ ከተማ 13 ተጨዋቾች ወደ ቡድኑ ተመልሰዋል
Next Article የፕሪሚየር ሊጉ የዳኞች ምደባና የዳኞቹ ውጤት ለዋጭ ስህተት አነጋጋሪ ሆኗል…

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ድንገተኛ ዜና

የውብ ጨዋታና የውጤታማ ቡድን አባት የሆነው አሠልጣኝ ስዩም አባተ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሸለበ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ነገ(ዓርብ)በሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ከቀኑ በ9:00ይፈፀማል።

hatricksport team By hatricksport team 7 years ago
ትግራይ ዋንጫ| ደቡብ ደርቢ ለፍፃሜ ያገናኘው ትግራይ ዋንጫ ነገ ፍፃሜውን ያገኛል
የዳኞቹ ተቃውሞ በርትቷል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ተወሰነ
የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ጨዋታዎች በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?