ከደመወዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ ከቡድኑ ካምፕ ወጥተው የነበሩት ተጨዋቾች ተመልሰው ለዛሬ ጨዋታ እየተዘጋጁ ነው።
ተጨዋቾቹ ከአዳማ ከተማ ጋር ዛሬ 9 ሰአት ለሚያደርጉት ጨዋታ ይዘጋጁ እንጂ ክለቡ ደመወዛቸውን በአስቸኳይ እንዲከፍላቸው በድጋሚ ጠይቀዋል። ለክለቡና ለደጋፊው ባላቸው ክብር ወደ ቡድን ቢመለሱም ደመወዛቸዌን ካልተከፈላቸው አቋማቸውን እንደማይቀይሩ በመግለጽ በአሰቸኳይ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። የተጨዋቾቹ መመለስ ቡድኑን ከመውረድ ለማትረፍ ሃላፊነቱን ለወሰዱት አሰልጣኝ ዘማሪያም
ወ/ጊዮሬጊስ ትልቅ እፎይታ የሰጠ ሆኗል።
በፕሪሚየር ሊጉ የ22ኛ ሳምንት ውጤት መሰረት ሻሸመኔ ከተማ በ13 ነጥብ 15ኛ ደፈጃ ላይ ይገኛል።