መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር ባወጣው የስራ ማስታወቂያ መሠረት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር ባወጣው የስራ ማስታወቂያ መሠረት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር ባወጣው የስራ ማስታወቂያ መሠረት መስፈርቱን ያሟሉ አምስት ተወዳዳሪዎች ባለፈው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል ለውድድር የቀረበውን የአንድ ዓመት የእግር ኳስ ልማት እቅድ አዘጋጅተው ገለፃ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

የፊፋ የቴክኒክ አማካሪ ዶሚኒክ ኒዮንዚማ በተገኙበት የተደረገውን ገለፃ ጨምሮ በስድስት የተለያዩ መመዘኛዎች (የስራ ልምድ ፣ የአሰልጣኝነት ላይሰንስ ፣ የትምህርት ዝግጁነት ፣ የእቅድ አዘገጃጀት ፣ የእቅድ አቀራረብና ጥያቄዎች የመመለስ ችሎታ እና ቃለ መጠይቅ) ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ተለይተው ታውቀዋል። በዚህም መሠረት

1ኛ – (ተመራጭ) – አቶ ዳንኤል ገብረማርያም
2ኛ – (ተጠባባቂ) – ዶ/ር ጌታቸው ቂናጤ
3ኛ – (ተጠባባቂ) – አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ ሆነዋል።

በውጤቱ መሠረት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት አቶ ዳንኤል ገብረማርያም በእግር ኳስ ሁለተኛ ዲግሪ ባለቤት ሲሆኑ የካፍ A ላይሰንስ ያላቸውና በተለያዩ ክለቦች የስራ ምልድ ያላቸው እንዲሁም በካፍ ኢንስትራክተርነት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በኣትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለዋጭ ስህተት ሰርቷል የተባለውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አሰልጣኝ ኤርሚያስ በቀለ እግርኳስ ፌዴሬሽኑን ከሰሰ…

አሰልጣኝ ኤርሚያስ በቀለ /ሮማሪዮ/ መብቴን ጥሷል ያለውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በመደበኛ ፍርድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ብሄራዊ  ዳኞች ኮሚቴ ዳኞችን የለየ ውሳኔን አሳልፈዋል

ኢንተርናሽናል አርቢትር ባህሩ ተካን በማሰናበት ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩን ባላየ ማለፉ አነጋጋሪ ሆኗል። ብሄራዊ...