መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡናና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ተጣምረዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡናና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ተጣምረዋል

አጋራ
አጋራ

👉የተጨዋቾች ምርጫው በአሰልጣኙ ጥቆማ ነው..

👉የደጋፊው ተቃውሞ ቀጥሏል…..

ኢትዮጵያ ቡና የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ የነበረውን አሰልጣኝ ተመስገን ዳና አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን የፊታችን ረቡዕ ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀሉትና የሚቀላቀሉት ተጨዋቾች በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ምርጫ መሆኑ ታውቋል። ኢትዮጵያ ቡና ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር ያለውን ውል ሃምሌ 30/2014 እንደሚያቋርጥ አሰልጣኙም በሀላፊነቱ የተረከባቸውን ንብረቶች እንዲመልስና የሀምሌ ወር ደመወዙም እንደሚከፈለው በመግለጽ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ ካስገባ ቀናቶች አልፈውታል።

በተለይ የአሰልጣኝ ካሳዬ ተተኪ የሚሆነው አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የመሆኑ መረጃ አፈትልኮ ከወጣ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን የፈረሙትና ይፈርማሉ የተባሉ ተጨዋቾች ክለቡን ያጠናክራሉ ብለው እንደሚያምኑ ነገር ግን አሰልጣኙ ላይ እምነት እንደሌላቸው በመግለጽ ጠንካራ የሆነ ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

የአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የአሰልጣኝነት ህይወት የሚጀምረው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመራ ከተመረጠበት 2010 ጀምሮ ነው። በ2011 የአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ምክትል ሆኖ ሀዋሳ ከተማን አሰልጥኗል። በ2012 የደቡብ ፖሊስ ዋና አሰልጣኝ ቢሆንም በኮቪድ ምክንያት ውድድሩ እስኪቋረጥ ሰርቶ 2013 ላይ እንደገና ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኑን ተረክቦ አንድ አመት ተኩል አሰልጥኗል። አሰልጣኙ በሴካፋ ከ20 አመት ሻምፒዮና ሁለተኛ የወጣበት ታሪኩ ትልቁ ሆኖ ተመዝግቦለታል። ከብሄራዊ ቡድኑ መልስ ወልቂጤ ከተማ የክለቡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት 12 ጨዋታ ከመራ በኋላ በመለያየታቸው አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን በመቅጠር የ2014 18 ጨዋታን እንዲመራላቸው በማድረግ የዘንድሮውን የውድድር አመት አጠናቋል።

አሰልጣኙ ለተመልካች በሚስበው ምርጥ አጨዋወት የሚታወቅ መሆኑ ትኩረት የሚስብ ሲሆን የቡናን ማራኪ አጨዋወት ያስቀጥላል ተብሎ በአመራሮቹ ታምኖበታል። ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር ህጋዊ ውል ያላሰሩት የቡናማዎቹ አመራሮች ግን የደጋፊዎቹን ጫና ፈርተው ሀሳባቸውን ይቀይራሉ ? ወይስ ? በጀመሩት አዲሱ ፕሮጀክት ይቀጥላሉ የሚለው ነገር በቀጣዮቹ 44 ሰአታት ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል።

ቡናማዎቹ በነገው ዕለት ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር ያላቸውን ውል ለማፍረስና የሀምሌ ወር ደመወዙን ከፍለው ሙሉ በሙሉ ለመለያየት ቀጠሮ መያዛቸው ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...