የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፉት ሳምንታት ሲያካሂድ የነበረውን የቴክኒክ ዳይሬክተርነት ፈተና አጠናቆ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ መመዘኛውን አሟልተዋል ያላቸውን አምስቱን ተወዳዳሪዎች የስራ ልምድ፣ ያላቸውን የአሰልጣኝነት ላይሰንስ፣ ያላቸው የትምህርት ደረጃ፣ የዕቅድና ኢንተርቪው ካየ በኋላ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማሪያምን በ81 ነጥብ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር እንዲሆን መርጦታል።
በውጤቱ መሠረት ዶ/ር ጌታቸው ቅናቴ 79.5፣አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ 77፣ አቶ ኩመራ በቀለ 72፣ አሰልጣኝ ታዬ ናኔቻ 71.5 እንዲሁም አቶ ፍሰሃ አገኘሁን 53.5 ውጤት ማግኘታቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ከአሸናፊው ከኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማሪያም ጋር በደመወዝና በጥቅማ ጥቅም ጉዳይ ይደራደራል ተብሎ ይጠበቃል።