የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መቐለ 70 አንደርታ የወቅቱ የተጨዋቾች የመስኮት ዝውውሩ 5ተኛ ና 6ተኛ ፈራሚዎቻቸውን አስታውቀዋል ።
አንደኛው ፈራሚ አብይ ተወልደ ይባላል።በ2011 በፈረሰው የመቐለ 70 አንደርታ ሁለተኛ ቡድን በአጥቂነት መጫወት የቻለው አብይ ቡድኑ በያዝነው ሳምንት የተሰጠውን የሙከራ ዕድል በመጠቀም የገብረመድህን ኃይሌን ስብስብ መቀላቀል ችሏል።
በተጨማሪ ምአም አናብስቶች አምና ዝዋይ ላይ በተካሄደው የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር 6 ግቦችን በማስቆጠር የውድድሩ ኮከብ ኣግቢነትን ከሌሎች ሁለት ተጨዋቾች ጋር የተጋራው ክብሮም አፅብሃ(ቺቻሪቶ) ከአብይ ጋር በተመሳሳይ በዚህ ሳምንት የተሰጠውን የሙከራ አድል በአግባቡ በመጠቀም ለመቐለ 70 አንደርታ መፈረሙን አረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
መቐለ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን አያከናወኑ ሚገኙት መቐለ 70 አንደርታዎች ቀጣይ 4 ቀናቶችን በበዓል ምክንያት ይበተናሉ።