ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞ ከእናንተ ጋር ልትገናኝ ስራዋን አጠናቃለች
ሀትሪክ በእትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምድ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተርና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ ከቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋች ሸዋረጋ ደስታ ጋር አዲስ ስለተቃቃመው የፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማህበር እና ሌሎች ከስፖርቱ ጋር በተገናኙ ድፍረት የተሞላባቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ቆይታን አድርጎ በድፍረት ምላሽ ተሰጥቶታል፤
ለሀትሪክ ሸዋረጋ ምን ብሎ ይሆን? ከምላሾቹ ውስጥ የሚከተሉት ይገኝበታል፡፡
-“ቀደም ሲል ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኞች ቅጥር በልካቸው ጃኬት ያሰፋ ነበር፤ አሁን ደግሞ የማህበራትን ድምፅ ነጥቆ ለራሱ በልኩ ጃኬት አሰፍቶ መልበስ ያማረው ይመስለኛል”
-“ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ድምጻቸውን ያለስስት ለሰጡት ማህበራት ድምፅ አለመሆኑና አለመታገሉ አሳዝኖኛል”
-“ችግሩ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ማቋቋሙ
ሳይሆን በፊት የነበረውን ማህበር ደፍጥጦ ወይም
ከስሟል የሚል ታቤላ መለጠፍ ሲጀመር ነው” የሚል ሲገኝበት ከእግር ኳሱና ከአትሌቲክሱ ጋር በተገናኘም ሌሎች መረጃዎችን ለምሳሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፌዴሬሽኑ
ፈተና የሆነ ጥያቄ ስለማቅረቡ
ቀነኒሳ በቀለ በአትሌቲክሱ ወደሚታወቅበት አሸናፊነት ስለመመለሱና በ2 ሰከንዶች ሪከርድ ባለመስበሩ ከ1.5
ሚሊዮን ብር በላይ ስለማጣቱ
አስቻለው ታመነ ቅ/ጊዮርጊስን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ልጠቅመው እፈልጋለው ብሎ ፊርማውን ስለማኖሩ እና
ወደ ግብፅ ሊግ ሳይሄድ ስለመቅረቱ በሀትሪክ ላይ ነገ የሚመለከቱ ይሆናል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም የዓለም ኮከብ ተጨዋችና አሰልጣኝ ስለሆኑት የርገን ክሎፕ እና ሊዮኔል ሜሲ እንደዚሁም ደግሞ ስለ አውሮፓ ሊግ ውድድሮችና ስለ አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጥሩ ጥሩ ዘገባዎችን የምታስመለክቶት ይሆናል፡፡ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞ ከእናንተ ጋር ልትገናኝ ስራዋን አጠናቃለች
Hatricksport team