ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን በዲሲፕሊኑና በታታሪነቱ የሚታወቀው አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና ፈራሚ ስዩም ተስፋዬ እንግዳችን ነው….በልምዱ ስፖርቱ የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን በማክበሩ ለረጅም ጊዜ መቆየቱን የሚናገረውና ኢትዮጵያ ከ31 አመት በኋላ ወደመሰረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ የቡድኑ አባል የነበረው ስዩም ተስፋዬ ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ”ዲሲፕሊን ሳታከብርና አንደበትህን ሳትቆጣጠር ለሰው ተምሳሌት መሆን አይቻልም” ሲል ተናግሯል።
*…. እስቲ እንጠይቃችሁ..? ለሚወዷት የነገዋ ሚስት ሽማግሌ ስትልኩ ተጨንቃችሁ አንደበት ያለው የሚያሳምን ሞገሱ በሙሽሪት ቤተሰቦች ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥረውን መርጣችሁ ነው…. የነገው አባወራ ሚስቱን መርቀው እንዲሰጡት የሀገር ባለውለታ የሆኑትን ሰዎች ሽማግሌ ከላከማ ነገሩ አበቃ…. የፋሲሉ የኋላ ደጀን አስቻለሁ ታመነም በዚህ በኩል ዘይዶ ተሳክቶለታል….
ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው፣ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ፣ አሰልጣኝ ውበቱ አባተና የቀድሞ መምህሩን ልኮ ፍቅሩን እንዲወስድ በሙሽሪት ቤተሰቦች ተፈቅዶለታል….
በዚህ ላይ ዘገባ ይዘናል…..
*…ምርጫ ያልሸፈነው ተጠባቂው የበርሊን ማራቶን….
….ቀነኒሳ በቀለ ለሌላ አዲስ ታሪክ የሚጠበቅበት የበርሊን ማራቶን የብዙዎችን ትኩረት ስቧል… ይስሃቅ በላይ ተመልክቶታል…
*… ከመሸሻ ወልዴ ጋር ቆይታ የነበረው የፋሲል ከነማው በረከት ደስታ 2014 እና 15ቱ ተጋጣሚዎቹ ላይ ፎክሯል….
“የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ደግመን እንወስዳለን” ሲልም አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥቷል…
*….አዳማ ከተማ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ከቀጠረ በኋላ ጥሩ የሚባሉ ዝውውሮችን እንዳደረገ ይነገራል አማኑኤል ጎበና ስለ ክለቡ መጻኢ ተስፋ ይናገራል….
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*…. ” ከ12 አመታት በኋላ ወደ ኦልድትራፎርድ የተመለሰውና ግብ አዳኝነቱን ያስመሰከረው ሪከርድ ሰባሪው ክርስቲያኖ ሮናልዶ “በማን.ዩናይትድ ሌላ አዲስ ታሪክ በድጋሚ ለማጻፍ ተዘጋጅቻለሁ”ሲል ተናግሯል..
የማዴይራው ልኡልን ቃለ ምልልስ ይዘናል….
*….የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜን ላየ የዛሬውን የስታምፎርድ ብሪጅ የቸልሲና የማን.ሲቲን ፍልሚያ ይናፍቃል…በዚህ ተጠባቂ ጨዋታስ ማን ይነግሳል? በጨዋታው ዙሪያ የተዘጋጀ መረጃዎችን አካተናል….
*…በሰሜን ለንደን አርሰናል ከቶተንሃም ሁሉም ሽንፈት የሚጠላበትን ፍልሚያ ነገ ምሽት በኤምሬትስ ያካሂዳሉ…..
የመድፈኞቹ አሌክሳንደር ላካዜት ገና ከአሁኑ ለቡድን ጓደኞቹ ማሳሰቢያ ሰጥቷል …..”በደርቢው ጨዋታም በማሸነፍ ለደጋፊዎቻችን የሚገባቸውን መስጠት አለብን” ሲል ተናግሯል።
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..
የመጀመሪያዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የቤስት ስፖርት አጋር
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……
አስተያየት ይስጡ