አቡበከር ናስር የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

የኢትዮጵያ ቡና እና የዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደምቆ ሲታይ በ በርካታ የአፍሪካ ክለቦች አይን ውስጥ ማረፍ ችሏል ።

በተለይም በዘንድሮው የውድድር ዓመት የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት ሪከርድ ይሰብራል ተብሎ ሲጠበቅ በዛሬው ዕለት የእውቅና ሽልማት እንደተበረከተለት ለማወቅ ተችሏል ።

አቡበከር ናስር በዛሬው ዕለት በ ቡናማዎቹ የቀድሞው ተጫዋች ሙሉአለም ጥላሁን የመጫወቻ ቁሳቁሶች በስጦታ መልክ እንደተሰጠው ታውቋል ።

📸natanim pictures

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ሙሉአለም ጥላሁን በአሁን ሰዓት ኑሮውን በሀገረ ጀርመን አድርጎ ሲገኝ ሽልማቱን በእህቱ ፀጋ ጥላሁን በኩል ቦሌ ብርሀኔ አደሬ ሞል በሚገኘው ሱቁ ለአቡበከር ናስር ማበርከት ችለዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor