” ብዙ ገንዘብ ሳናወጣ ዘንድሮም ሻምፒዮን
እንደምንሆን አረጋግጥላችኋለሁ”
አቶ ንዋይ በየነ
/የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ጸሃፊ/
ራሱን በገቢ ለማጠናከር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአመት 5 ሚሊዮን ብር የሚያገኝበትን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ከጸሀይ ባንክ ጋር ተፈራረመ።
ሁለቱ ወገኖች በፈጸሙት ስምምነት መሰረት በየአመቱ አስር በመቶ የሚያድግ የ5 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያደርግ ሲሂን ለክለቡ የልምምድ ቦታ ልማትም ሆነ ግንባታ ባንኩ እስከ 40 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የረጅም ጊዘለ ብድር የሚያመቻች ይሆናል። በውሉ መሰረት ደጋፊዎች አካውንት ሲከፍቱ ከተከፈተው ሂሳብ ላይ ተቀናሽ ተደርጎ 10 ብር ለክለቡ ወዲያውኑ አስተዋጽኦ ያደርጋልም ተብሏል።
- ማሰታውቂያ -
በስምምነቱ መሰረት ክለቡም ደጋፊዎቹ የአባልነት ክፍያዎች በባንኩ በኩል እነረዲከፍቱ፣ ለተጨዋቾችና ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ በባንኩ በኩል ይደረጋል፣የክለቡ ቲሸርትና የስታዲየም መግቢያ መኪትና በባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሸጥ እንደሚደረግና ሌሎች ጥቅሞች ይፈጸማሉ ተብሏል።
በዚህ መግለጫ ላይ የተገኙት የክለቡ የቦርድ ጸሃፊ አቶ ንዋይ በየነ ” ተፋላሚዎቻችን ግራ እስኪገባቸው ድረስ ጠንክረን በርካታ ገንዘብ ሳናወጣ ዘንድሪም ሻምፒዮን እንደምንሆን አረጋግጥላችኋለሁ” በማለት ተናግረዋል
የሁለቱ ወገኖች ስምምነትን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማህበር የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀልና የጸሃይ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ መስፍን በፊርማቸው አጽንተውታል።